1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል መንግሥት ምስረታ 75ኛ ዓመት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 17 2015

ከ75 ዓመታት በፊት በይፋ የተቋቋመውን የእስራኤል መንግሥት ለመመስረት የታገሉትንና የሞቱትን ለማስታወስ ዛሬ ለመታሰብያ በሃገሪቱ ሲረንስ ተሰማ። የመታሰቢያው በዓል እስራኤል ዛሬ ማክሰኞ ምሽት የምታከብረዉን የነፃነት ቀንዋን ቀደም ብሎ ነዉ ነዉ የሚከበረዉ። እስራኤል ነፃነቷን ያወጀችዉ በጎርጎረሳዉያኑ 1948 ዓ.ም የዛሬ 75 ዓመት ነዉ።

75 Jahre Israel
ምስል Eyal Warshavsky/SOPA Images via ZUMA Press Wire/picture alliance

 

ከ75 ዓመታት በፊት በይፋ የተቋቋመውን የእስራኤል መንግሥት ለመመስረት የታገሉትንና የሞቱትን ለማስታወስ ዛሬ ለመታሰብያ በሃገሪቱ ሲረንስ ተሰማ። የመታሰቢያው በዓል እስራኤል ዛሬ ማክሰኞ ምሽት የምታከብረዉን የነፃነት ቀንዋን ቀደም ብሎ ነዉ ነዉ የሚከበረዉ። በያዝነዉ ዓመት እስራኤል በጎርጎረሳዉያኑ 1948 ዓ.ም ነፃነቷን ያወጀችበት 75 ዓመት ይደፍናል ። እስራኤል እንደ ሃገር ከመሰረተች በኋላ ወዲያውኑ በግብጽ፣ በኢራቅ፣ በዮርዳኖስ፣ በሊባኖስ እና በሶሪያ ጦር ጥቃት ጥቃት ደርሶባታል። በዚህ በአረብና በእስራኤል ጦርነት ወቅት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን መኖርያቸዉን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋል።

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW