የእስራኤል አዲስ የስደተኞች ረቂቅ ህግ22 ኅዳር 2007ሰኞ፣ ኅዳር 22 2007ምንም እንኳን በግብፅ በኩል አድርገው በህገ ወጥ መንገድ ወደ እስራኤል የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር፣ ባለው ጥብቅ ቁጥጥር የተነሳ ቢቀንስም፣ አሁን ድረስ በእስራኤል 48 000 የአፍሪቃ ስደተኞች እንደሚገኙ ይታመናል።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግምስል picture-alliance/dpaማስታወቂያ በተደጋጋሚ እስራኤል የሚገኙ ስደተኞች ፤ሀገሪቱ በቂ ተገን እንደማትሰጥ ሲያማርሩ ተሰምተዋል። ትናንት የእስራኤል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያፀደቀው አዲስ የስደተኞች ረቂቅ ህግ ምናልባት የስደተኞቹን ይዞታ በመጠኑም ቢሆን ያቃልላል የሚል ዕምነት አለ። አዲሱ ረቂቁ ምን እንደሚያካትት እየሩሳሌም የሚገኘውን ወኪላችን ዜናነህ መኮንንን በስልክ አነጋግረንዋለሁ። ዜናነህ መኮንን ልደት አበበ