እንዲህ እንዳሁኑ ዘመን ተቀይሮ በየ10 ሜትሩ በቅመም ያበደዉ የህንድ እና የቻይና ምግብ አዳራሽ ተወዳጅ ሳይሆን፣ ከሰማንያ በላይ ብሄር ብሄረሰቦችን የያዘችዉ የኢትዮጻያ የተለያዩ ጣዕም ያላቸዉ ባህላዊ ምግቦችም በአዉሮጻዉያን ዘንድ ተወዳጅነታቸዉ ታዋቂነታቸዉ በመጉላት ላይ ይገኛል፣ የዛሪዉ የባህል መድረካችን በለንደን ሆርን አፍሪካ ፉድ በተሰኘ የኢትዮጽያን ምግብ ከሚያስተዋዉቁ ባለሞያ ወይዘሮ ጋር ያስተዋዉቀናል መልካም ቆይታ።