የእንሰሳት ሕክምናና ምርምር
ረቡዕ፣ ነሐሴ 25 2008ማስታወቂያ
ትምህርት ክፍሉ በዘመናዊ ቤተ- ሙከራዎች የተደራጀ ሲሆን በርካታ ችግር ፈቺ ምርምሮችን በማካሄድ ላይ እንደሆነም ተገልፆአል። ከምርምሮቹ አንዱ ደግሞ ከብቶች መኖ በሚገኝበት ወራት ብቻ እንዲወልዱ የሚያደርግ ምርምር እንደሆነ ነዉ የተመለከተዉ። «ሲንክሮናዜሽን» በሚል መጠርያ የሚታወቀዉ ይህ ምርምር ከብቶች የሚወልዱበትን ጊዜ ወስኖ ላምዋን «ሆርሞን » በመቆጣጠር በተፈለገዉ ወራት አርግዛ በተፈለገዉ ወራት እንድትወልድ የሚያደርግ መሆኑ ነዉ የተነገረዉ። መቀሌ የእንስሳ ሕክምና ኮሌጅ የተገኘዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን የኮሌጁን ዲንና ተመራማሪ ዶ/ር በሪሁ ገብረኪዳንን አነጋግሮ ሰፋ ያለ መሰናዶ ልኮልናል።
ዮኃንስ ገ/እግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ