1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእንቅስቃሴ እገዳ በጀርመን

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 19 2014

የጀርመን የፌደራልና የክፍለ-ግዛቶች መሪዎች ባሳለፉት ዉሳኔ መሰረት የተከተቡም ሆነ ያልተከተቡ ሰዎች ለግል ድግስ ከ10 በላይ ሆነዉ መሰብሰብ አይችሉም።የስፖርት ማዘዉተሪያ፣ሲኒማ፣ ምግብና መሸታቤቶች ዉስጥ የሚስተናገደዉ ሰዉ ቁጥርም ገደብ ተጥሎበታል

Deutschland | Ministerpräsidentenkonferenz | Corona-Pandemie | PK
ምስል Bundesregierung/dpa/picture alliance

የጀርመን መንግስት የኮሮና በተለይም ኦሚክሮን የተባለዉ አዲስ ልዉጥ ተሕዋሲ ስርጭትን ለመከላከል የጣለዉ የእንቅስቃሴና የግንኙነት ገደብ ከዛሬ ጀምሮ ፀንቷል።የጀርመን የፌደራልና የክፍለ-ግዛቶች መሪዎች ባሳለፉት ዉሳኔ መሰረት የተከተቡም ሆነ ያልተከተቡ ሰዎች ለግል ድግስ ከ10 በላይ ሆነዉ መሰብሰብ አይችሉም።የስፖርት ማዘዉተሪያ፣ሲኒማ፣ ምግብና መሸታቤቶች ዉስጥ የሚስተናገደዉ ሰዉ ቁጥርም ገደብ ተጥሎበታል።ገደቡ የተጣለዉ በተለይ በጎሪጎሪያኑ የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በየከተማዉ አደባባይ የሚሰበሰበዉ ሕዝብ በተሕዋሲዉ እንዳይለከፍ ለመከላከል ነዉ።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW