1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ስምምነት

ሐሙስ፣ ጥር 20 2013

የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች  ከቀናት በፊት በክልሎቹ ፕሬዚዳንቶች በኩል ስላደረጓቸው ስምምነቶች የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን ለዶይቸ ቬለ አብራርተዋል።

Äthiopien Ibrahim Usman
ምስል Mesay Tekelu/DW

ሁለቱ ክልሎች ከአንድ ሺህ አራት መቶ ኪ.ሜ በላይ በድንበር ይጋራሉ

This browser does not support the audio element.

የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች  ከቀናት በፊት በክልሎቹ ፕሬዚዳንቶች በኩል ስላደረጓቸው ስምምነቶች የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን ለዶይቸ ቬለ አብራርተዋል። በሶማሌ እና ኦሮሚያ የተደረገው ስምምነት አይነት ከአዋሳን የአፋር ክልል ጋርም ወደፊት ሊደረግ እንደሚችል ተጠቊሟል። 

ከአንድ ሺህ አራት መቶ ኪ.ሜ በላይ በድንበር የሚዋሰኑት የኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ከቀናት በፊት የሁለቱን ክልል አዋሳኝ ህዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች በጋራ ለመስራት ስምምነት መድረሳቸውን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን ገለፁ ፡፡ሰምምነቱ የሁለቱን ክልል ህዝቦች የቆየ ወንድማማችነት ለማጎልበት ያለመ መሆኑንም ለDW በስልክ  በሰጡት መግለጫ ጠቁመዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የስምምነቱ የትኩረት መስክ ያሏቸውን ነጥቦችም ጠቁመዋል፡፡ በሁለቱ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ላለፉት ጊዜያት ሲፈጠሩ በነበሩ ግጭቶች የህዝብ ግንኙነት ላይ ችግር ሲፈጠር እንደነበር በመጥቀስ አሁን ያሉ ተጨባጭ ሁኔታዎችን በሚመለከት ጥያቄ ያቀረብኩላቸው አቶ ኢብራሂም ተከታዩን ምላሽ ሰተዋል፡፡

በሌላኛው አቅጣጫ ከአፋር ክልላዊ መስተዳድር ጋር በሚዋሰነው የሶማሌ ክልላዊ መስተዳድር በየጊዜው ግጭቶች መፈጠራቸውን በማንሳት አሁን ከኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ጋር የጋራ ለውጥ ለማምጣት የተደረሰው ዓይነት ስምምነት የማድረግ ሀሳብ ስልመኖሩም ለምክትል ርዕሰ መስተዳድር  ኢብራሂም ዑስማን ጥያቄ አቅርቤላቸው ተከታዩን ብለዋል፡፡

ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሚሰሩ ስራዎችን የሚሰራ ፅ/ቤት በጋር መቋቋሙን እና በቀጣይም በተጎራባች አካባቢዎች ለግጭት መንስዔ የሚሆኑ ችግሮችን በመለየት ስራ እንደሚሰራ ተገልፃል፡፡ የሁለቱ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ ተገናኝተው የጋራ ስምምነቱን መፈራረማቸው የሚታወስ ነው፡፡  
መሳይ ተክሉ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW