የኦሮሚያ ሰላምና የሸማቂዎች ማንነት
ረቡዕ፣ የካቲት 2 2014![Ethiopia, Addis Abeba | Oromia PP reaction on OFC withdrawal from the coming election](https://static.dw.com/image/56770910_800.webp)
ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል በብሔር የተቧደኑ ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈፅሙት አሰቃቂ ግድያ፣ግፍና ማፈናቀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ነዉ።ጥቃቱ የሚደርስበት ነዋሪና ስለአካቢዉ የሚያዉቁ ተንታኞች እንደሚሉት በተለይ ኦነግ ሸኔና የአማራ ፅንፈኛ ቡድን የሚል ስም የተሰጣቸዉ ታጣቂዎች በወለጋ ምዕራብ ጉጂና፣ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ዉስጥ የሚገድሉና የሚያፈናቅሉት ሕዝብ ቁጥር፣ የሚዘርፉት ሐብት መጠንም እየናረ ነዉ።የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነርም ታጣቂዎቹ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ማድረሳቸዉን አልካዱም።ባለስልጣኑ «ፅንፈኛ» ባሏቸዉ በሁለቱ ቡድናት ላይ እርምጃ በመውሰድ የነዋሪዎችን ሰላም ለመመለስ ብርቱ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋልም ፡፡
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ