1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሚያ ክልል አዲስ ዞን ያስከተለዉ ዉዝግብ

ሐሙስ፣ መጋቢት 14 2015

ሰሞነኛውን ውሳኔ በመቃወም በጉጂ ማህበረሰብ በኩል ጥያቄ እያቀረቡ ከሚገኙ የማህበረሰብ ተወካዮች ጂሎ ዲቤ የተባሉ የጉጂ ተወላጅ በበኩላቸው ህብረተሰቡ የሚያነሳው ጥያቄ መቋጫና አሳማኝ ምላሽ ባላገኘበት መንግስት የነበረውን የጉጂ ዞን መዋቅር በማፍረስ አዲሱን ዞን ወደ ተግባር ማስገባት ጀምሯል ይላሉ፡፡

Shakiso Town
ምስል Yidnekachew Gashaw

«አስተዳደርን ማዋቀር የመንግስት ኃላፊነት ነዉ»ቃል አቀባይ

This browser does not support the audio element.

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባለፈዉ ወር ከቦረና፣ ጉጂ እና ባሌ ዞኖች ዘጠኝ ወረዳዎችን አገናኝቶ አዲስ ያዋቀረዉ ምስራቅ ቦረና  ዞን  አሁንም እያወዛገበ ነዉ።የባሌ እና የጉጂ ተወካዮች እንደሚሉት አዲሱ አስተዳደራዊ መዋቅር  ለመንግስት ያቀረቡት ጥያቄ ተገቢ መልስ ሳያገኝ አዲሱ ዞን  ስራ ጀምሯል ይላሉ።የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በበኩሉ የአስተዳደራዊ ዞን መዋቅሩ የአስፈጻሚ አካል ሚና እንደመሆኑ የተለየ የፖለቲካ ፍላጎት ተደርጎ መነሳት አልነበረበትም ብሏል፡፡

“በጉጂ እና ቦረና ማህበረሰብ መካከል “ነጌሌ-ቦረና” በመባል ስትጠራ በነበረው ከተማ ላይ በነበረው ውዝግብ አለመግባባቱ ለ20 ዓመታት ያህል የቀጠለ ነው፡፡ ነገሌ የጉጂ ዞን ዋና ከተማ ሆና ያገለገለችም ለ20 ዓመታት ያህል ነበር፡፡ በዚህ ውስጥ እኛ ለምን የመስዋዕት በግ ለመሆን እንደተገደድን አይገባንም፡፡ በርግጥ አቶ ለማ መገርሳ ኦሮሚያን ሲያስተዳድሩ በነበረበት ጊዜ የዛሬ አራት ዓመት ገደማ ደቡብ ምስራቅ ባሌ በሚል እዚህ መዳወላቡ አከባቢ ከባሌ ሳንወጣ ዞን እንዲመሰረትልን ጥያቄ አቅርበን ነበር፡፡ ጥያቄያችን ያ ሆኖ ሳለ ሶስት ወረዳዎችን ምንም ባላወቅንበትና ባልተወያየንበት ሁኔታ ከዚህ ቆርጠው ምስራቅ ቦረና ያሉት ዞን ውስጥ ነው ያካተቱብን፡፡ እኛ ገዳችን ሲኮመንዶ ነው፡፡ ስርዓቱን እዚህ መዳወላቡ እና ኦዳ ሮባ ነው የምናከናውነው፡፡ የአርሲና ባሌ መሬት አጠቃላይ በዚህ ገዳ ነው ስርዓቱን የሚከውነው፡፡ የቦረና እና ባሌ ዞኖች ወሰን በገናሌ ነው የሚወሰነው፡፡ አሁን ግን ገናሌን ተሻግረው ሀረናቡሉቅ፣ ኦቦርሶ እና መዳወላቡ ወደ ነገሌ ቦረና ተካሏል ተቀበሉ አሉን፡፡”ተቃውሞ በአዲሱ የኦሮሚያ ክልል አስተዳደራዊ ወሰን

ይህን አስተያየት የሰጡን ሰሞነኛውን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዲስ አስተዳደራዊ መዋቅርን ተከትሎ 21ኛ ዞን ምስራቅ ቦረና በሚል ሲመሰረት ከባሌ ዞን ወደዚያ የተቆረጡ ሶስት ወረዳዎች አግባብነት ላይ ቅሬታቸውን የገለጹ የሲኮመንዶ አባገዳና የአገር ሽማግሌ ኢብራሂም ሀጂ-መሃመድ ናቸው፡፡ ማህበረሰቡ ዱብዳ ሆኖበታል ያሉትን ውሳኔ በይሁኝታ እንዳልተቀበለው የገለጹት አስተያየት ሰጪው፤ አባገዳዎች እና የአገር ሽማግሌዎች የማህበረሰቡን ቅሬታ ይዘው ወደ ተለያዩ የመንግስት መወቅር ቢያመሩም እስካሁን መፍትሄ አልመጣም ብለዋል፡፡

ምስል Yidnekachew Gashaw

“እኛ መጀመሪያ ለጥያቄ ያመራነው ወደ ባሌ ዞን አስተዳዳሪ ነው፡፡ ማህበረሰቡ ውሳኔውን እንዳልተቀበለ በሰላማዊ ሰልፍ እና በተለያዩ መንገዶች መግለጹም ይታወቃል፡፡ ለዞን አስተዳዳሪው ቅሬታችን ስናቀርብ ከክልሉ የተወከሉም አምሰርት ሰዎች መጥተው አነጋግረውን ነበር፡፡ የሲኮ መንዶ አባገዳዎች ከአርሲም ከባሌም በዚህ ውይይት ላይ ተሳትፈን ቅሬታችን ስንገልጽላቸው፤ ወደ ሌላ ዞን ወደ ቦረና ዞን ህደን እንዴት ነው የገዳ ስርዓታችንን የምንከውነው ብለናል፡፡ ይህ ከአራት ዞን ጋር ስለሚያጣላችሁ አቁሙ ጥያቄያችን መልሳችሁ መዋቅሩን ማቆም ካልቻላችሁ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንትም ጋር አገናኙን፤ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሄደን ጥያቄያችንን እናቀርባለን ብለናቸው ባለመስማማት ነበር የተለያየን፡፡ አሁን ግን ውሳኔውን ተቀበሉ ብለውን ዞኑን እያዋቀሩ ነው፡፡”

ሰሞነኛውን ውሳኔ በመቃወም በጉጂ ማህበረሰብ በኩል ጥያቄ እያቀረቡ ከሚገኙ የማህበረሰብ ተወካዮች ጂሎ ዲቤ የተባሉ የጉጂ ተወላጅ በበኩላቸው ህብረተሰቡ የሚያነሳው ጥያቄ መቋጫና አሳማኝ ምላሽ ባላገኘበት መንግስት የነበረውን የጉጂ ዞን መዋቅር በማፍረስ አዲሱን ዞን ወደ ተግባር ማስገባት ጀምሯል ይላሉ፡፡”የነበረው መዋቅር ፈርሷል፡፡ አዳዲስ ሹማምንቶች በአዲሱ ዞን ላይ ተሹሟል፡፡ በነገሌ የነበረው የጉጂ ዞን መዋቅርና አስተዳዳሪዎቹም ወደ አዶላ እንዲዛወሩ ጊፊት እየተደረገ ነው፡፡ የጉጂ ማህበረሰብ ግን አሁንም ነገሌ የጉጂ ዞን ዋና ከተማ እንደሆነች በማመን ለዚያው ነው የሚታገለው፡፡ መንግስት ጉዳዩን አቅልሎ ሳያይ ተገቢውን ምላሽ ብሰጠው መልካም ይመስለናል፡፡ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠትም ጥያቄውን በተገቢ አኳኃን ወርዶ ማየት ያስፈልጋል” ነው ያሉት፡፡

በጉጂ ዞን የቀጠለው የአዲስ አስተዳደራዊ ዞን ምስረታ ተቃውሞ

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ግን የአዲሱ 21ኛ ዞን ምስረታ ያስፈለገው የአስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍና ለህዝቡ ጥቅም ነው ይላል፡፡ ዶይቼ ቬለ ቅሬታ ስላስነሳው የአዲሱ ዞን ምስረታን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረበላቸው የክልሉ ኮሚዩኒኬስን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ኦሮሚያ እንደክልል ሲመሰረት 8 ዞኖች ብቻ እንደነበሩ አስታውሰው ዞኖቹን አመቺ በሆነ መልክ የማዋቀሩ ኃላፊነትም ሆነ ስልጣን የክልሉ አስፈጻሚ አካል ነው ሲሉ መልሰዋል፡፡ “የኦሮሞ ህዝብ በባለም ተካለለ በቦሌ ያው ኦሮሚያ ነው፡፡ አንድ መንግስት ነው ያለው፡፡ መንግስት አስፈላጊ ነው ብሎ ባመነ ጊዜ መዋቅሩን ፈትሾ ማደራጀት ይችላል፡፡ ወስኖ ማወያየትም ሆነ አወያይቶ መወሰን ይቻላል፡፡ ሲለዚህ ልማትን፣ መልካም አስተዳደር እና ፀጥታን ተደራሽ ማድረግ ነው የአዲሱ መዋቅር ዝርጋታ አስፈላጊነት፡፡ የትም ተካለለ የትም ከመንግስት የሚፈለገውን አገልግሎት ማግኘት ነው አስፈላጊው ነገር፡፡ ስለዚህ መንግስት የማስፈጸም አቅሙን ማዕከል በማድረግ የሚያደርገውን የመዋቅር ዝርጋታ ከፖለቲካ ጋር ማገናኘት አስፈላጊ አይደለም” ብለዋል፡፡

ሥዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW