1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሚያ ክልል የሰላም ጥሪ ጉጉትና አስቻይ አውዱ

ሥዩም ጌቱ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 30 2016

በኦሮሚያ ክልል ዓመታትን የፈጀውና ከፍተኛ ቀውስ ያስከተለው ግጭት ማብቂያ እንዲያገኝ ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጥሪ አቀረቡ ። ራሱን «የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት» ያለውና መንግስት «ሸኔ» ያለው የታጠቀው ቡድን በፊናው ለመንግስት የሰላም ጥሪ ምላሽ ሲሰጥ፤ ነገሩን ሐቀኛ ሰላም ከመሻት የመጣ አይደለም በማለት አጣጥሎታል ።

የኦሮሚያ ክልል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ። ፎቶ፦ ከማኅደር
የኦሮሚያ ክልል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ። ፎቶ፦ ከማኅደርምስል Seyoum Getu/DW

የኦሮሚያ ክልል «የሰላም ጥሪ»ና ምላሽ

This browser does not support the audio element.

በኦሮሚያ ክልል ዓመታትን የፈጀውና  ከፍተኛ ቀውስ ያስከተለው ግጭት  ማብቂያ እንዲያገኝ ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጥሪ አቀረቡ ። ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ታጥቀው ለሚንቀሳቀሱ አካላትም የትጥቅ አውርዱ ጥሪ በማሰማት ሰላም ይውረድ ብለዋል ። በኦሮሚያ በስፋት ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው ራሱን «የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት» ያለውና መንግስት «ሸኔ» ያለው የታጠቀው ቡድን በፊናው ለመንግስት የሰላም ጥሪ ምላሽ ሲሰጥ፤ ነገሩን ሐቀኛ ሰላም ከመሻት የመጣ አይደለም በማለት አጣጥሎታል ። አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡ አንድ የሰላምና ደህንነት ባለሞያ ግን፦ ሰላም አማራጭ የሌለው መንገድ በመሆኑ ተፋላሚ ኃይሎች እንታገልለታለን ለሚሉት ሕዝብ ሲሉ ሰላም ማውረድ አለባቸው ብለዋል ።  

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከሰሞኑ በይፋዊ ማኅበራዊ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ዘለግ ባለው ጽሑፍ ከአንድ ሳምንት ያነሰ እድሜ የቀረውን አዲስ ዓመትና የተስፋ ጮራ የሚፈነጥቅበትን ወርሃ መስከረም «በሰላም እንቀበል» በማለት ሰፋ ያለውን ሐሳባቸውን ዘርዝረውበታል ።

አቶ ሽመልስ  "የ2017 ዓ.ም. የኦሮሞ ሕዝብ የተከበረው ባህል የኢሬቻ በዓል ዋዜማ ያሳለፍነውን የምናገናዝበበትና ተሃድሶ የምናካህድበት መሆን ይገባል” ነው ያሉት፡፡ በዚህን ወቅት "ለህዝባችን ሰላሙ ይመለስ” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለአንድነት፣ ለተስፋ ጮራ መፈንተቅና አንዱ ሌላውን ለመረዳት ጊዜው አሁን ይሁን ሲሉም ጥሪያቸውን አሰምተዋል፡፡

በዚህ ጥሪያቸውም "የኦሮሞ ህዝብ ዛሬን ያየው ብርቱ ፈተና ውስጥ በማለፍ ነው” ያሉት አቶ ሽመልስ "የኦሮሞ ትግል የደረሰበትን ደረጃ ያልተገነዘበ- አረም” ያሉት ኃይል በጠመንጃ አፈሙዝ የህዝቡን ነገ ለአደጋ ዳርጎ፣ ባህሉንና እሴቱንም ሰብሎ የህዝቡን የመልማት መብት አደናቅፏል ነው ያሉት፡፡ አቶ ሽመልስ አከሉ፤ አርሶ አደሩን በማማረር፣ ንግድን በማደናቀፍ የህብረተሰቡ የመልማት ፍላጎትን ከናካተው ማኮላሸት እንዴት የኦረሞ ህዝብ ግብ ሆናል? ሲሉም ጠየቁ፡፡

«የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት» ምላሽ

እራሱን የኦሮሞ ነጻዊት ሰራዊት ያለውና መንግስት "ሸኔ” እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በፊናው ትናንት ለዚሁ ለርዕሰ መስተዳድሩ ረዘም ያለ ጽሁፍ በሰጠው መልስ ደግሞ የርዕሰ መስተዳድሩን አስተያየቶች "ቀልድ” በማለት አጣጥሎታል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ። ፎቶ፦ ከማኅደርምስል Seyoum Getu/DW

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሦስተኛ ድግሪ እጩና የሰላምና ደህንነት ባለሙያ እንዲሁም የክልሉን ፖለቲካዊ ሁናቴዎች በቅርበት የሚከታተሉት አቶ መብራቱ ገርጂሶ  በኦሮሚያ የሚፋለሙት የመንግስት አካላት እና የታጣቂ ቡድን አመራሮች ውዝግቡ አሁንም የሰላም ምእራፉ ገና ያልቀረበ መሆኑን ፍንጭ የሚሰጥ ነው ይላሉ፡፡ "በኦሮመኪያ ከተቀሰቀሰ ስድስት ኣመታትን የተሻገረውን ይህን ግጭት ለመፍታት በተለያዩ የመንግስት አካላት ትሪ ስስተጋባ ስና ይህ መጀመሪያው አይደለም” የሚሉት አቶ መብራቱ ብንስ ለጊዜው በሁለቱ ተፋላሚዎች መካከል የመቀራረብ አዝማሚያ አለመኖሩን እተመለከትን ነው ብለዋል፡፡ "ምናልባት ግን ሁለቱ አካላት የግል ፍላጎታቸውን ገተው ሀቀና መነጋገር ማድረግ ከቻሉ ሰላም የመምታት እድል ይኖረዋል” ያሉት የሰላምና ደህንነት ባለሙያው ተፋላሚ ሃላቱ ካለፈው ስህተቶች ታርመው ሁነኛ መፍትሄ ካልፈለጉ ለሁለቱም አካላት፣ ለህዝብና ለሀገርም ምናልባት የሰቆቃውን እድሜ የሚያስቀጥል እድል ሊያስቀትል እንደምችል አስረድተዋል፡፡

የሰላሙ አስፈላጊነት፤ የሚሰርተዋል ቁርተንነት?

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ መንግስታቸው አሁን ለሰላም እድል ለመስጠት ካለው መሻት "በሰላማዊ መንገድ መግባት ለሚፈልግ የታጠቁ አካል ጥሪ እያቀረብን ነው” ብለዋል፡፡ የትኛውም የታጠቀ ኃይል መፍታት እንዳለበት እናምነት ያሉት ሽመልስ "የተሰጠውን የሰላም አማራጭ ገፍቶ የህዝቡን ሰቆቃ ማራዝም ምርጫው ባደረገ ኃይል ላይ ግን የህግ የበላይንት የማስከበር እርምጃ ይቀጥላል” ነው ያሉት፡፡ እክለውም ሰላም አማራጭ የሌለው መንገድ በመሆኑ 1000 ኪ.ሜ. መሄድ ብያስፈፈልገው 999.99 ያህሉን ሄደን ለማሳካት ዝግጁ ነን ነው ያሉት፡፡

ኦነግ-ኢነሰ ግን በበኩሉ ለርዕሰ መስተዳድሩ በሰጠው ምላሽ በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ላይ የተቃጣው የመንግስት ጥቃት ይህን አያሳይም ይላል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ለእስር እና ለመበታተን መዳረጋቸውንና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፈኮ) አመራሮችም ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት ተመሳሳይ እጣ እንደደረሰው በጽሁፉ አስረድቷል፡፡ ከታንዛንያው ድርድር መልስ የኦነግ-ኦነሰ አመራሮች ወዳገር እንዳይመለሱ መንግስት እክል ፈጥሮ እንደነበርም የከሰሰው መግለጫው የሚቀርበውን የሰላም ጥሪ ከሃቅ ያል ሆነ በማለት አጣጥሎታልም፡፡

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፈኮ) ጽ/ቤትምስል Seyoum Getu/DW

የሰላም እና ደህንነት ባለሞያ አቶ መብራቱ ግን አሁንም በትልቁ መታሰብ ያለበት አርሶ አገር የሚመግበው አርሶ አደር ሰላሙን በማጣቱ ወደ ቀዬው ከመመለስ ይልቅ ችግሩ እንዳይባባስ ነው ይላሉ፡፡ "ህዝቡ በአደባባይ እየጠየቀ ያለው ጦርነት መገዳደሉ ይብቃን ሰላም ናፈቀን ነው፡፡ በዚያ ላይ ጎረቤት አገር የጸጥታ ችግር እያንዣበበ በመሆኑ የአገር ውስጥ መቆራቆዝ ማብቂያ ሊያገኝ ይገባል” በማለት አርሶ አደሩ በሰላም ማረስ የሚችልበት መንገድ መፈለግ እንዳለበትም መክረዋል፡፡

ሥዩም ጌቱ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW