የኦሮሚያ ጸጥታ፤ ተስፋ እና ተግዳሮቱ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 22 2017በኦሮሚያ ክልል በተለይም በማዕከላዊ የክልሉ አከባቢዎች ታጣቂዎች በስፋት ገብተዋል ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ የፀጥታ ይዞታው ይረጋጋ ይሆናል በሚል ተስፋም አሰንቆ ነበር፡፡ ከተለያዩ ከነዚህ አከባቢዎች አስተያየቶቻቸውን የሰጡን የየአከባቢዎቹ ነዋሪዎች የቀደመ ተስፋቸው አሁን ድረስ እንኳ አብሯቸው የዘለቀ አይመስልም፡፡ ግጭት አለመረጋጋቱ ከመሻሻል ይልቅ ጠንክሯል በሚል በአከባቢው ማህበረሰብ ከሚገለጽባቸው አንዱ ሰሜን ሸዋ ዞን (ሰላሌ) ነው፡፡
በዞኑ የያያ ጉሌሌ ወረዳ አስርተያየት ሰጪ እንደሚሉ አሁንም ድረስ ከተስፋ ይልቅ ስጋቱ እንዳየለ አለ፡፡ አስተያየት ሰጪው ለዚህም ሃሙስ ታህሳስ 10 ቀን 2017 በአከባቢያቸው ተከሰተ ያሉትን ማሳያ በማቅረብ ነው ሃሳባቸውን መግለጽ የጀመሩት፡፡
በምስራቅ ሸዋ ዞን አደዓ ወረዳ የተፈጸመ እገታ እና ግድያ
“በቀለ ሰርቤሳ የሚባል አንድ ሰው ተገድሎ ነው በሜዳ አውረ በልቶት ምኑም የጠፋው፡፡ እኚ ሰው በወረዳችን አመራር ላይ ነበር፡፡ አሁን በተደራጀው የቀበሌ መዋቅርም በአደረጃጀት ላይ ተመድበው በስራ ላይ ነበሩ፡፡ ማታ ሶስት ሰዓት ሳይሞላ ከቤቱ ተወስዶ ነው በዚያው በቤቱ ደጃፍ የተገደለው፡፡ ማታ እንደተገደለ ጠዋት ብፈለግ ምኑም የለም አውሬ በልቶታል” ነው ያሉት፡፡
የጠነከረው ስጋት
አስተያየት ሰጪው በአከባቢቸው የጸጥታው ይዞታ ከመረጋጋት ይልቅ ጠንክሮ ማስጋቱን እንደገፋበትም በአስተያየታው አክለዋል፡፡ “አረ ምንም መረጋጋት የለም፡፡ ሰው ፍርሃት ውስጥ ነው፡፡ በኛ አከባቢ መረጋጋት አለ ብለህ የምትጠቅሰውም ስፍራ የለም፡፡ ገጠር አከባቢ እንደተለመደው ነው፡፡ ይባስ ብሎ አሁን ከተማ ላለነውም ሰው ስጋት ውስጥ ነው ያለው” ብለዋል፡፡
ከታጣቂዎቹ መግባት ጋር ተያይዞ ሰው እፎይታ ተሰምቶት ነበር ያሉን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቶሌ ወረዳ ነዋሪ በፊናቸው በዚህ ወረዳ እና በአዋሳኞቹ አከባቢ የሰዎች በከንቱ መገደልና አለመረጋጋት አላቧራም ባይ ናቸው፡፡ አስተያየት ሰጪው እንዳውም ንጹሃን መኖሪያቸው ድረስ ሌሊትም ጭምር እየሄዱ ጥቃት በሚፈጽሙባቸው የታጠቁ አካላት የሚገደሉበት ክስተቶች መበራከታቸውን አመልክተዋል፡፡
ታጣቂዎች በብዛት የገቡናቸዉ የኦሮሚያ ክልል እና ጸጥታው - የነዋሪዎች አስተያየት
“ሁሉም ብታረቅ፡፡ ታጣቂዎችም ብገቡ ጦርነት የሰለቸው ህዝብ ፍላጎት ነው” ያሉት አስተያየት ሰጪው የህዝቡ አሁናዊ ቀዳሚ ፍላጎት ሰላምና ሰላም ብቻ ብሆንም ንጹህ ሰው መገደሉ እንዳላበቃ በአስተያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
የጸጥታው ይዞታ ውስብስብነት
ከምስራቅ ሸዋ ዞን አደዓ ወረዳ ጊጬ ገረባቦ ከተባለ የገጠር ቀበሌ አስተያየታቸውን የሰጡን ነዋሪ በፊናቸው ከጸጥታው ስጋት የተነሳ ቤት እንኳ የሚያድር ሰው እየጠፋ ነው ባይ ናቸው፡፡ “የሚገርምህ ቤተሰብ ውጪ ነው የሚያድረው፡፡ አሁን ድረስ ወጣቶችን ጨምሮ ማንም ሰው ውጪ ነው የሚያድረው፡፡ መንግስት በመሃል ለማረጋጋት ሞክሮ ነበር ግን ከዚያም በኋላ አስቸጋሪ ሁኔታ እንደተፈጠረ አለ” ብለዋል፡፡
ሌላው በቅርቡ ተደጋጋሚ ጥቃቶች በተበራከቱበት አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ አሁንም ተደጋግሞ ጥቃት የሚፈጸምበት ማህበረሰብ በእርግጠኝነት ያሸውን ቦታ የሚዘዋወርበት አውድ እንደሌሌ የአከባቢው ነዋሪ አስተያየት ሰጪ አንስተዋል፡፡ “ዝምብሎ የመዋዛት ነገር 15 ቀን አንድ ወር ክፍረተት እየሰጠ እያዘናጋ ነው ጥቃቱ የሚከሰተው” ባይ ናቸው፡፡
አንድ ዓመት ያለፈው የአከባቢው አለመረጋጋት ከስር መሰረቱ እልባት ተገኝቶለት እንደማውቅም የገለጹት የአከባቢው ነዋሪ፤ “ምንግስትም እኮ የመከላከል አይነት ነገር ነው እንጂ ዘልቆ ገብቶ እርምጃ የወሰደበት የለም፡፡ ለዚህ ደግሞ ትልቁ ችግር ታጣቂ ተብሎ ህዝብ ላይ ጥቃት የሚፈጽሙት የማህበረሰቡ አካል ናቸውና ለመለየት ለመንግስትም አዳጋች ነው የሆነው” በማለት የዚህ አከባቢ የግጭት ባህሪ ከሌላው አከባቢ እንደምለይ አስረድተዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ለሰላም ጥሪ የቀረበባቸው ሰልፎች
በኦሮሚያ ክልል በስፋት የምንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ-ኦነሰ) በቅርቡ መንግስት ከሰራዊቱ አንድ ክንፍ ጋር ያደረገውን ስምምነት ክፉኛ በመንቀፍ “ጭቾሚና” ያለውን ሰፊ የጥቃት ዘመቻ መክፈቱን ባለፈው ሳምንት አሳውቆ ነበር፡፡
ዶይቼ ቬሌ በክልሉ ወቅታዊ የጸጥታ ይዞታ ላይ ተጨማሪ ማባራሪያዎች እና እልባቶቹን በተመለከተ ለመጠየቅ ለክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ብደውልም ስልካቸው ባለመነሳቱ አስተያየታቸውን በዚህ ዘገባ ማካተት አልተቻለንም፡፡
ሥዩም ጌቱ
እሸቴ በቀለ
ታምራት ዲንሳ