1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የማህኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ዓርብ፣ ነሐሴ 8 2012

ዝናሽ ወርቁ በእገዳው ቅር መሰኘታቸውን ነው በፌስቡክ ያሰፈሩት።«መደመር እየተባለ መቀነስ አስፈላጊ አይደለም ኦቦ ለማ ህዝብ ውስጥ ገብተዋል።እና ይህ ሲሰማ ቅር ያሰኛል።አንድነታችሁን  ማየት እንፈልጋለን።»ሲሉ

Äthiopien Lemma Megersa, Verteidigungsminister
ምስል፦ Prime Minister Office, Addis Ababa

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ መከላከያ ላከያ ሚንስትር አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ ሦስት የኦሮምያ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች "ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት በጊዜያዊነት" መታገዳቸው ከሰሞኑ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አነጋጋሪ ጉዳዮች ዋነኛው ነበር።በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ  አመራሮች መካከል የተነሳው ውዝግብም በማህበራዊ መገናና ዘዴዎች ልዩ ልዩ አስተያየቶችን ያስተናገደዱ የሰሞኑ ኹነት ነው። 
የኦሮምያ ብልጽግና ፓርቲ ነሐሴ 2 እና ነሐሴ 3 ፣2012 ዓም ባካሄደው ጉባኤ ፍጻሜ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነበር ሦስት ከፍተኛ አመራሮቹ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት በጊዜያዊነት መታገዳቸውን ይፋ ያደረገው።እሁድ ማምሻውን ፓርቲው በሰጠው መግለጫ የታገዱት የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ፣ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ዶክተር ሚልኬሳ ሚዴጋንና ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን መሆናቸውን አስታውቋል።ወይዘሮ ጠይብ ሀሰን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሲሆኑ ዶክተር ሚልኬሳ ደግሞ የኦሮምያ ብልጽግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አማካሪ ነበሩ።የእገዳውን ዜና በርካቶች በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተቀባብለውታል።ልዩ ልዩ አስተያየቶችም ተሰንዝረውበታል። 
ራስ ዳሸን በሚል የፌስቡክ ስም የታመመውን  ማከምና ማዳን ተመራጭ ነው።የማይድን ከሆነ ግን በሽታው ወደ ጤነኛውም እንዳይሰራጭ በጊዜ ቆርጦ ማስወገዱ ሁለተኛው የተሻለ አማራጭ ነው።በማለት ሃሳባቸውን አካፍለዋል።ዝናሽ ወርቁ ደግሞ በእገዳው ቅር መሰኘታቸውን ነው በፌስቡክ ያሰፈሩት።«መደመር እየተባለ መቀነስ አስፈላጊ አይደለም ኦኖ ለማ ህዝብ ውስጥ ገብተዋል።እና ይህ ሲሰማ ቅር ያሰኛል።አንድነታችሁን ማየት እንፈልጋለን።»ሲሉ  
«የብልጽግና ስራ መሾምና መሻር ብቻ ሆነ ሰላም የለም ፤ተስፋም የለም፤ ይጀምራሉ አይጨርሱም፣ ይዘራሉ አያጭዱም ምን ዓይነት ጉድ ነው።ነውጥ አለ፣ ለውጥ ግን የለም።»ካሉ በኋላ መፍትሄም የሚጠቁሙት ደግሞ ሁንዳኦል ቶላ ናቸው ።«መፍትሄው ይቅር መባባል ነው።ሁሉም ጥፋተኛ ነው።አንዱን ከሶ አንዱን መሸለም አይቻልም።ስለዚህ ይቅር ተባብለን ብንኖርስ ሲሉ ሃሳብ አቅርበዋል።
።«እኔ የማምንበትን በድፍረት ለመናገር የምፈራ ሰው አይደለሁም አብራራለሁ እገልጻለሁ አስረዳለሁ እኔና ዶክተር ዐቢይን የሚለየን ሞት ብቻ ነው።» ሲሉ አቶ ለማ ከዚህ ቀደም የተናገሩት በትዊተር ያሰፈሩት ገነት ያዕቆብ፣ ለለማና ለዐቢይ ጥያቄ ያቀርባሉ። ከሁለታችሁ ማን ሞቶ ነው የተለያያችሁት?ሲሉ።
 መሐሪ «ለማ እኮ ሲጀመር የብልፅግና አባል አይደለም ወገን ተረጋጉ እንጂ ፣በራሱ ፍቃድ ነዉ የወጣዉ ሲሉ ሣራ መሐመድም ሲጀመር ለማ ብልፅግና ውሥጥ አልነበረም ከየት ነው የታገደው?ብለዋል።
ሰሎሞን ወጋየሁም ይጠይቃሉ«ለመሆኑ አቶ ለማ መገርሳ የብልጽግና አባል ናቸው እንዴ አሁን ታገዱ የሚባለው?ግን አቶ ለማ መገርሳን በቀላሉ መርሳት አይቻልም?ባለውለታ ናቸው መልካሙን እንመኝላቸዋለን። 
ሌላው በዚህ ሳምንት የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎችን ትኩረት የሳበ ጉዳይ የኦነግ አመራሮች ውዝግብ ነው።የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሃምሌ 19 እና 20፣2012 ዓም ካካሄደው አስቸኳይ የማዕከላዊ ኮሚቴ  ስብሰባ በኋላ በአመራሮቹ መካከል የተነሳው ውዝግብ እንደቀጠለ ነው።በዚህ ሳምንት የግንባሩ ሊቀመንበር በአቶ ዳውድ ኢብሳ ፈርመውበታል በተባለ መግለጫ ስድስት የግንባሩ አመራሮች ለጊዜው ከስራ መታገዳቸው ሲያነጋግር ከርሟል። ታግደዋል የተበሉ አመራሮችም የግንባሩ ምክትል ሊቀመንበርን ጨምሮ ያለ ሊቀመንበሩ ይሁኝታ በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው እና ሰኞ እለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት ናቸው፡፡በውዝግቡ ላይ በማህበራዊ መገናና ዘዴዎችልዩ ልዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል። 

ምስል፦ DW/Seyoum Getu
ምስል፦ picture-alliance/AA/M. W. Hailu

ሀሰን አሊ አህመድ «የኦሮሞ ህዝብ ንቃ ከዚህ በላይ ምን ማስረጃ አለ እነዚህ ሰዎች ድሮም ለህዝብ ሳይሆን የሚታገሉት ለስልጣን ነው የሆነስ ሆነ እና መጀመሪያ እራሳቸው ያልተስማሙ እንዴት ነው ሌላውን አስማምተው የሚመሩት።»ብለዋል 
በአጭሩ«ድሮም የሥልጣን እንጂ የዓለማ አንድነት የላቸውም ያሉት ሳንዲፕ ኩማር ናቸው።
የሸሪፍ አባገላን የፌስቡክ አስተያየት ዘለግ ያለ ማብራሪያ አካቷል« የዕድሜ የአካልና ቁመት አለመመጣጠን የጤና ችግር ነው ።ገና ከእናት ሆድ እያለና ተወልዶ እስከ ሁለት አመት ድረስ በምግብ የተጎዳ ህፃን ዕድሜ ልኩን በቅንጨራ የጤና ችግር እየተጎዳ ይኖራል ።ኦነግ ዕድሜውና ዕድገቱ በፊፁም አይመጣጠንም ።ዕድሜው ወደ ግማሽ ምዕተ አመት ይጠጋል። የፖለቲካም ሆነ የጦር ብቃቱና ዕድገቱ ደግሞ በተቃራኒ የቀነጨረ ነው ።ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ይሄው ዛሬ ድረስ አመራሩ በመከፋፈልና መባላት ይሰቃያል ። 
ጉበና ፈንታውም ተቀራራቢ አስተያየት ነው የሰጡት።«መቼም ቢሆን የብሔር ፖለቲካ ሠለም አያመጣም ምክኒያቱም አመሠራረቱ ከጥላቻ ከተበድያለሁ ትርክት በሌላው ላይ የበላይ ለመሆን በማሠብ ሲሆን ብሔራቸውን በስሜት ነድተው መጨረሻ ላይ የግል ስልጣን እና ዘረፋ ላይ የሚሠማሩ በመሆኑ እነሡም አይስማሙም ለሀገርም ሰላም አያመጡም።»በማለት 
ድባቤ ሰይፉ«መጀመሪያ ውስጣችሁን ሳታጠሩ ይህንን ጨዋ ህዝብ እንመራለን ብላችሀ ጫካ መኖራችሁ ማንነታችሁን ወለል አድርጎ ለህዝባችን አሳየልን ፤ እንኳንም ምርጫው ሳይደርስ ፍላጎታችሁን ለህዝቡ አሳያችሁት ወጣቱን ለናንተ ሲባል ስትማግዱት ኖራችሁ ጊዜው ደረሰና መሰንጠቅ ጀመራችኋ።ብለዋል። 
ያሲን አህመድ ጊራጋን «ይሄ ነው አመራር ጀግንነት ጀል ዳውድ አንበሳ !!»ሲሉ አወድሰዋቸዋል። 
በኦነግ በማዕከላዊ ኮሚቴው ስብሰባ እና በሂልተኑ የድርጅቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተሳተፉት የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ ለዶይቼ ቨሌ እንደተናገሩት እሳቸውን ጨምሮ ሌሎች አምስት አመራሮች ላይ እግድ ያስተላለፈው መግለጫ፣ የሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ይሁኝታ ያለው ነው። እገዳው የድርጅቱን ህጋዊ መሰረት ያላሟላ በመሆኑ ተግባራዊ አይሆንም ነው የሚሉት፡፡

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW