1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሞ ህዝብ ሰቆቃ እንዲያበቃ መንግስት እና ኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በእርግጥ ፍላጎት አላቸውን?

እሑድ፣ ኅዳር 15 2017

በኦሮሚያ ክልል በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሚደረግ ግጭት እና ጦርነት መቀጠሉ የህዝቡን መከራ እና ሰቆቃ አባብሶታል። የጦርነቱ ገፈት ቀማሽ የሆነው ህዝብ ፤ ግድያ እና መፈናቀልን ጨምሮ ጦርነቱ ያደረሰበት ቀውስ እንዲያበቃ በአደባባይ ድምጹን አሰምቷል።

Kombobild | Jiregna Gudeta | Ayana Feyisa | Hailu Adugna

የኦሮሞ ህዝብ ሰቆቃ ማብቂያ ያገኝ ይሆን ? ተፋላሚዎች ተስፋ ይሰጡት ይሆን ?

This browser does not support the audio element.

በኦሮሚያ ክልል በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሚደረግ ግጭት እና ጦርነት መቀጠሉ የህዝቡን መከራ እና ሰቆቃ አባብሶታል። የጦርነቱ ገፈት ቀማሽ የሆነው ህዝብ ፤ ግድያ እና መፈናቀልን ጨምሮ ጦርነቱ ያደረሰበት ቀውስ እንዲያበቃ በአደባባይ ድምጹን አሰምቷል።

በመንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል ከአንድም ሁለት ጊዜ ከሀገር ውች የተሞከረው የሰላም ንግግር አልሰመረም ። ህዝቡ ተፋላሚዎች ለሶስተኛ ጊዜ ተገናኝተው ችግሩን በሰላም ይፈታሉ ብሎ በሚጠብቅበት በአሁኑ ወቅት ሁለቱም ወገኖች በየራሳቸው መንገድ የአስገዳጅ የአዳዲስ ወታደር ምልመላ እና አፈሳ እያከናወኑ ነው በሚል ስሞታ ይሰማል። ይህ ደግሞ የሰላም ጥሪ የሚሳተጋባውየኦሮሚያ ግጭት መወሳሰብ፡ የንጹሃን እልቂትና መከራን የክልሉን ነዋሪ ተስፋ ከማሳጣት አልፎ ክልሉን ብሎም ሀገሪቱን ለተጨማሪ የቀውስ ዓመታት እንዳይጋብዝ አስግቷል።

የኦሮሚያ ግጭት መወሳሰብ፡ የንጹሃን እልቂትና መከራ

የኦሮሞ ህዝብ ስቃይስ እስከ መቼ በዚህ አይነት ሁኔታ ይቀጥላል ? ከህጻን እስከ አዛውንት ሴት እና ወንድ ሳይለይ የእርሻ በሬ ፣ ሞፈር እና ቀንበር ይዞ አደባባይ በመውጣት ለሰላም የተጣራው ህዝብ ጥሪስ ስለምን ጆሮ ዳባ ልበስ ተባለ?  

የኦሮሚያውን ግጭት ማስቆሚያ መፍትሄው ምንድነው ?

የሳምንቱ የእንወያይ ዝግጅታችን የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ፤ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ዋና አዛዥ ዋና አማካሪ ጂሬኛ ጉደታ እንዲሁም የፖለቲካ ተንታኙ አቶ አያና ፈይሳ ጋብዞ አወያይቷል።

ታምራት ዲንሳ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW