አንድ-ለ-አንድ፤ ከኦነሠ አማካሪ ከጃል ጅሬኛ ጉዳታ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 3 2017
ማስታወቂያ
አንድ-ለ-አንድ ከኦነሠ አማካሪ ከጃል ጅሬኛ ጉዳታ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
የኢትዮጵያ መንግስት መከላከያ ጦር አማራ ክልል ከፋኖ፣ ኦሮሚያ ክልል ደግሞ ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) ጋር የገጠመዉ ዉጊያ በሐገሪቱ በተለይም በሁለቱ ክልሎች የብዙ ሰዎች ሕይወት እያጠፋ፣ ብዙ ነዋሪዎችን እያፈናቀለ፣ ከፍተኛ የምጣኔ ሐብት ቀዉስም እያስከተለ ነዉ።የአማራ ክልልን ዉጊያ ለማስቆም እስካሁን በግልፅ የተደረገ ድርድር የለም።በኦሮሚያ ክልል ለረጅም ዓመታት የቀጠለዉ ዉጊያን ለማስቆም ግን ከዚሕ ቀደም ሁለት ጊዜ ታንዛኒያ ዉስጥ በኢትዮጵያ መንግስትና መንግሥት ኦነግ ሸኔ በሚለዉ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) ተወካዮች መካከል ድርድር ቢደረግም ተፋሊሚዎች ባለመስማማታቸዉ ዉጊያዉ ቀጥሏል። የዉጊያዉን ሒደት፣ የሚያደርሰዉን ጥፋትና ለሰላም ያለዉን ተስፋ በተመለከተ የኦነሠ አማካሪ ጃል ጅሬኛ ጉደታን የዛሬዉ የአንድ-ለአንድ ዝግጅታችን እንግዳ አድርገናቸዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ