1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ለሕወሃት ኃይሎች የሰጠው ማሳሰቢያ

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 27 2014

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) “ህወሀት ወደ ኦሮሚያ ክልል የሚያደርገውን ጉዞ” እንዲገታ ጠየቀ፡፡ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች በተስፋፋው የትግራዩ ጦርነት ሕወኃት ሰሞኑን በአማራ ክልል ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞችን ተቆጣጥሮ ወደ መሃል አገር እንደሚገፋ አሳውቆ ነበር፡፡

 Logo Oromo Liberation Front

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ የሕወሃት ኃይሎች ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዳይገቡ አሳሰበ

This browser does not support the audio element.

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) “ህወሀት ወደ ኦሮሚያ ክልል የሚያደርገውን ግስጋሴ” እንዲገታ ጠየቀ፡፡

ከሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መንግስት የተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ ወዲህ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች በተስፋፋው የትግራዩ ጦርነት ሕወኃት ሰሞኑን በአማራ ክልል ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞችን ተቆጣጥሮ ወደ መሃል አገር እንደሚገሰግስ አሳውቆ ነበር፡፡ይህንኑን ተክትሎም ነው ኦነግ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ሕወኃት “የኦሮሞ ህዝብን ሉዋላዊነት እንዲያከብር እና የጦር ሀይላቸውን ወደ ኦሮሚያ ድንበር ውስጥ ከማስገባት እንዲቆጠቡ” ሲል ያሳሰበው።የፓርቲው ቃል አቀባይ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ አሁን ላይ በትግራዩ አማጺያን እና መንግስት መካከል የሚካሄደውን ጦርነት ትርጉም አልባ በማለት የሚደረጉ የክተት ጥሪዎችንም ነቅፈዋል፡፡

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW