የኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት የሕዝብ አስተያየት
ዓርብ፣ ሐምሌ 17 2007ማስታወቂያ
ዋና ዋና መንገዶች ለጊዜዉ እንደሚዘጉ የገለፁት ባለስልጣናት ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያዉም እንዲሁ እሳቸዉን የያዘዉ አዉሮፕላን ሲደርስም ሆነ የኬንያ ጉብኝታቸዉን ፈፅመዉ ወደ ኢትዮጵያ በሚጓዙበት ሰዓትም እንደሚዘጋ ገልጸዋል። ሳፋሪኮም የተሰኘዉ የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅትም በኦባማ ቆይታ ወቅት አገልግሎቱ ችግር ሊገጥመዉ እንደሚችል ከወዲሁ ለደንበኞቹ ጠቁሟል። ናይሮቢ ላይ በሚካሄደዉ የንግድ ጉባኤ የሚገኙት ኦባማ እሁድ ዕለት ወደኢትዮጵያ ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት አስመልክቶ የሕዝብ አስተያየት አሰባስበናል።
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ