1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦብነግ በምርጫዉ እንደሚሳተፍ አስታወቀ 

ረቡዕ፣ ኅዳር 3 2012

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ሃገራዊ ግንባር ሆኖ እንደሚሰራ አስታወቀ። ድርጅቱ ከሰሞኑ ለአንድ ሳምንት ጎዴ ከተማ ላይ ባካሄደው ጠቅላላ ስብሰባውም የቀድሞ ሊቀመንበሩ ሽሮ አዲስ መሪ መርጧል።

Mitglieder der ONLF/Ogaden National Liberation Front
ምስል Getty Images/A.Maasho

አዲስ ሊቀመንበርም መረጠ

This browser does not support the audio element.

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ሃገራዊ ግንባር ሆኖ እንደሚሰራ አስታወቀ። የትናቱን ዜናችንን ያደመጣችሁ እንደምታስታዉሱት ኦብነግ አንጋፋዉን የግንባሩን ሊቀመንበር ሽሮ አዲስ ሾሟል፤ ዓርማዉን ለወጧልም። ላንድ ሳምንት ያክል ጎዴ-ሶማሌ መስተዳድር የመከረዉ ጉባኤ ለ21 ዓመት ግንባሩን በመሩት በአድሚራል መሐመድ ዑመር ዑስማን ምትክ የቀድሞዉን የግንባሩን ዋና ፀሐፊ አብዱረሕማን ሼሕ ማሪንን ሊቀመንበሩ አድርጎ መርጧል። የግንባሩ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀሰን ሙዓሊን ለድሬዳዋዉ ወኪላችን መሳይ ተክሉ በስልክ አንደነገሩት ግንባሩ እስካሁን በሚጠቀምበት አርማ ላይ የነበረዉ የክላሺንኮቭ ምስል በእስኪሪብቶና ንስር እንዲለወጥ ጉባኤዉ ወስኗል። የድሬዳዋዉ ወኪላችን መሳይ ተክሉ የግንባሩን ቃል አቀባይ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል። 

መሳይ ተክሉ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW