1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦነግ መግለጫ ፤ የሰላማዊ ዜጎች ጥቃት

ዓርብ፣ ጥር 17 2016

ስለመግለጫው አስተያየታቸውን የሰጡት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ፤ በተለይም በወረዳው ጉቢሶ ቀበሌ ተፈጽሟል ያሉት የአየር ላይ ጥቃት በርካታ የቤት እንስሳት ማለቃቸውንም ገልጸዋል፡፡ መጠነ ሰፊ ጉዳቶች የደረሱት በሰላሌ እና ደቡብ ምዐወራብ ሸዋ ዞን ነውም ብለዋል፡፡ጥቃቱ የተፈጥሮ ሃብትንም ያወደመ ነበር” ነው ያሉት፡፡

ጉጂ ዞን፤ ኦሮምያ ክልል
ጉጂ ዞን፤ ኦሮምያ ክልል ምስል Private

«በኦሮሚያ መንግሥት በሚካሄዳቸው ዘመቻዎች ንጹሃን ዜጎች የጥቃት ሰለባ እየሆኑ ነው»

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሚያ በተለያዩ አከባቢዎች ታጣቂዎችን ለማደን በሚያደርገው ዘመቻ ንጹሃን ዜጎች ሰለባ እየሆኑ ነው ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ወቀሰ፡፡
ፓርቲው ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው የመንግስት ሰራዊት በንጹሃን ላይ “ዘግናኝ” ያለውን ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገልጿል ስዩም ጌቱ ተጨማሪ ዘገባ አለው
እንደ ፓርቲው መግለጫ በመንግስት ይወሰዳል በተባለው የምድር እና የሰው አልባ የአየር ጥቃት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ በሰሜን ሸዋ (ሰላሌ) እና ጉጂ ዞኖች ሰላማዊ ዜጎችም ላይ ጥቃት ተፈጽሟል፡፡ የኦነግ መግለጫ የመንግስት ጦር በዘመቻው ከባባድ መሳሪያዎችን እና ቦምቦችን ስጠቀም ሰላማዊ ዜጎች ሰለባ ይሆናሉ ይላል፡፡ 
የፓርቲው መግለጫ አክሎ እንዳብራራው ከአራት ቀናት በፊት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በያያ ጉሌሌ ወረዳ ቂንዶ አገምሶ በተባለ ቀበሌ አምስት ሰዎች ተገድለው ሁለት ሰዎች ክፉኛ ተደብድበዋል፡፡ የተጎጂዎችን ስም ዝርዝር ያስቀመጠው የኦነግ መግለጫ የስድስት ሰዎች ቤት መቃጠሉንም ነው የገለጸው፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አርማምስል Seyoum Getu/DW

 

በተመሳሳይ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቀርሳ ማሊማ ወረዳም በመንግስት ጦር ተፈጽሟል በተባለው የአየር ጥቃት ሰላማዊ ዜጎችና የቤት እንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን ፓርቲው አሉኝ ካላቸው የመረጃ ምንጮት ማረጋገጡን ነው ያመለከተው፡፡ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ
ስለመግለጫው አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ፤ በተለይም በወረዳው ጉቢሶ ቀበሌ ተፈጽሟል ያሉት የአየር ላይ ጥቃት በርካታ የቤት እንስሳት ማለቃቸውንም ገልጸዋል፡፡ 


“መጠነ ሰፊ ጉዳቶች የደረሱት በሰላሌ እና ደቡብ ምዐወራብ ሸዋ ዞን ነው፡፡ ጥቃቱ ከሰውም ህይወት በተጨማሪ የተፈጥሮ ሃብትንም ያወደመ ነበር” ነው ያሉት፡፡
ፓርቲው በመግለጫው በጉጂ ዞንም አዶላ ሬዴ አቦላ በተባለ ቀበሌም ተፈጽሟል ባለው የአየርና የየብስ ጥቃት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አመልክቷል፡፡ 
የኢትዮጵያ መንግስት ግን በተለያዩ ጊዜያት በሚሰጣቸው መግለጫዎች ንጹንን በውጊዎች መሃል ተጠቂ እንዳሆኑ እንደሚሰራ ይገልጻል፡፡

ከኦሮምያ የተፈናቀሉ ሰዎች በአማራ ክልልምስል Alemenew Mekonnen/DW

 

የኦሮሚያው ግጭት፡ የቀድሞ ተዋጊዎች የታህድሶ የኦሮሚያው ግጭት፡ የቀድሞ ተዋጊዎች የታህድሶ ስልጠናከዚሁ ጋር ተያይዞ የመረጃችሁ ምንጭ ምን ያህል ተጨባጭ ነው የተባሉት የኦነግ ቃል አቀባዩ አቶ ለሚ ገመቹ “በአከባቢው ያሉ የድርጅታችን የመረጃ ምንጮች እና የተለያዩ ተጠቂ የማህበረሰብ አካላትን በምንጭነት ስለምንጠቀም ትክክለና የመረጃ ምንች ላይ እንመሰረታለን” ብለዋል፡፡
ስለኦሮሞ ነጻነት ግንባር ክስ ዶይቼ ቬለ ለተለያዩ የመንግስት አካላት ደውሎ ማረጋገጪ አሊያም ማስተባበያ ለማግኘት ጥረት አድርጓል፡፡ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሚዪኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አብዶ ተፈጽሟል ስለተባለው ጥቃት የሰሙት መረጃም ሆነ የሚያውቁት ነገር እንደሌሌ ገልጸዋል፡፡ ስለ ጉዳዪ ለመጠየቅ ለመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር እና ለኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊዎችም ደውለን ምላሻቸውን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልሰመረም፡፡ 

ስዩም ጌቱ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW