1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦነግ ሠራዊት የትጥቅ ማፍታት አለመፍታት ጉዳይ

Merga Yonas Bula
ረቡዕ፣ መስከረም 30 2011

በኢትዮጵያ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ከጥቂት ጊዜ በፊት ወደ አገር የተመለሰው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ሠራዊት ትጥቅ መፍታት ወይም አለመፍታት ጉዳይ ሰሞኑን ብዙ ማነጋገር ይዟል።

 Logo Oromo Liberation Front

የኦነግ ሰራዊት የትጥቅ ማፍታት አለመፍታት ጉዳይ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ አስመራ ኤርትራ ተጉዞ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ባነጋገረበት ወቅት ግንባሩ ወደ አገር ተመልሶ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልን እንድያደርግ የቀረበ ጥሪ እንጂ ትጥቅን መፍታት ጉዳይ እንደ «አጀንዳ» የተነሳ እንዳልነበረ የመ/ ኮ/ ጉ/ ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል። ትጥቅ ይዞ ሰላማዊ ትግል ማካሄድ እንደማይቻልም አቶ ካሳሁን አክለው ገልፀዋል።

ኦነግ ትጥቅን  አስፈትቶ 1300 የሚሆኑ ሰዎች በአሮምያ ክልል በአርሲ ዞን አርዳይታ የተሀሃድሶ ስልጠና በመከታተል ላይ እንደሚገኙ አቶ ካሳሁን ተናግረዋል።

«ኦነግ ወደ ሀገር የገባው ትጥቅ ፈትቶ ነው፣ የቀረውን ትጥቁንም  መፍታት አለበት፤ ካልሆነ መንግስት ትጥቅ የማስፈታቱን ስራ ይሰራል» የሚለዉን የመንግሥት አቋም  የኦነግ አመራር እንዴት እንደሚመለከተው «DW» ላቀረበው ጥያቄ፣ የኦነግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ የልዑኩ መሪ እንዲሁም የድርድሩ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ኢብሳ ነገዎ ሲመልሱ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ «በሚድያ  ከመከራከር» ጉዳዩን የሚከታተል የተዋቀረዉ ኮሚቴ ቢመለከተው እንደሚሻል ገልጸው፣ ጦሩ ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ በምን ዓይነት አኳሁዋን አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ መንግስትና በኦነግ መካከል የሚደረገዉን ዉይይት ለመከታተል የተቋቋመዉ ስምንት አባል ያለዉ ኮሚቴ በሚቀጥሉት ቀናት በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመምከር ሊገናኝ እንደሚችል የኮሚቴዉ አባል አቶ ኢብሳ ተናግረዋል። ትጥቅ መፍታት ወይም አለመፍታት የድርድሩ አካል ባይሆንም በሂደት የሚፈታ ጉዳይ ነዉ  ሲሉ አቶ ኢብሳ ገልፀዋል።

መንግስት ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ከሱ ቁጥጥር ውጭ የሆኑ አካላት እንዲኖሩ እንደማይፈልግ  በኦክስፎርድ ዩኒቬርስት በአፍሪቃ ጥናት ማዕከል ተመራማሪ ጄይሰን ሞስል ለ«DW» ተናግረዋል። ስለዚህ መንግስት ያለዉ አማራጭ ይህን አለመግባባት ማስወገድ ወይም የታጠቀዉን ኃይል ትጥቅ ማስፈታት ይሆናል ብለዋል። «ለእኔ እውነተኛ ጥያቄ ከኦነግ ጋር የተቆራኙ ፖለቲከኞች  ክልሉን ከሚመራ የኦሮሞ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ ጋር አብረው ይሰራሉ ወይም ከሂደቱ ዉጭ በመሆን የተቃዉም ፖለቲካ ፓርቲ ሆነው ይቀጥላሉ የሚለው ነው። ታጣቂ ቡድን ሆነው መቀጠል አያዋጣቸውም።   ታጣቂ ሆኖዉ ከቀጥሉ  ራሳቸውን ከፖለቲካው ሂደት ያገልላሉ።» 

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW