1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግሥት 3 የኦነግ አመራሮች እና ሁለት ጋዜጠኞችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይልቀቃቸው

ማክሰኞ፣ መጋቢት 29 2012

የኦነግ ስራ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ባቲር ፊሌ ፣ የፖለቲካ ጉዳዮች ተጠሪ ገዳ ገቢሳ ፣ የግንባሩ አባል የሆነው ቢሊሱማ አራርሳ እንዲሁም የONN ምክትል ዳይሬክተር ደሱ ዱላ እና ጋዜጠኛ ዋቆ ኖሌ ፍርድ ቤቱ በወሰነላቸው መሠረት ከእስር ሊፈቱ ይገባል

Logo von Amnesty International

አምንስቲ መንግሥት ያሰራቸዉን ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ ጠየቀ

This browser does not support the audio element.


ፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ በሰጠባቸው እና ውሳኔውን ሳያስፈጽም ከሳምንት በላይ በእስር ያቆያቸውን 3 የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራሮች እና ሁለት ጋዜጠኞችን መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቃቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ተቋም አምንስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ። አምንስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው ማግለጫው እንዳለው የኦነግ ስራ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ባቲር ፊሌ ፣ የፖለቲካ ጉዳዮች ተጠሪ ገዳ ገቢሳ ፣ የግንባሩ አባል የሆነው ቢሊሱማ አራርሳ እንዲሁም የONN ምክትል ዳይሬክተር ደሱ ዱላ እና ጋዜጠኛ ዋቆ ኖሌ ፍርድ ቤቱ በወሰነላቸው መሠረት ከእስር ሊፈቱ ይገባል ብሏል። መግለጫውን በተመለከተ በአምንስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ ኣካባቢ ጉዳዮች አጥኚ አቶ ፍሰሐ ተክሌን ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ከኬኒያ በስልክ አነጋግሬአቸኋለሁ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW