1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኦነግ አቤቱታና የብልጽግና ፓርቲ መልስ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 12 2013

ኦነግ ትናንት 10 (አስሩም) አባላቶቹ በመንግስት የፀጥታ አካላት ተወስደው መታሰራቸውን አብራርቷል፡፡የፓርቲው ጊዜያዊ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እርምጃውን ብልጽግና ፓርቲ በኦነግ ላይ የከፈተው ዘመቻ አካል ብለውታል።የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ቃል አቀባይ አቶ ታዬ ደንደአ ግን ክሱን አጣጥለዋል።

 Logo Oromo Liberation Front

የኦነግ አቤቱታና የብልጽግና ፓርቲ መልስ

This browser does not support the audio element.

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መንግስት የድርጅቱን አመራሮች እና የፓርቲው ልሳን ሚዲያ ሙያተኞችን አስሮብኛል ሲል አማረረ፡፡ፓርቲው ባወጣው መግለጫ "በመንግስት የፀጥታ አካላት ታፍነው ተወስደዋል" ያላቸው ስምንት የፓርቲው አመራር አባላት እና ሁለት የኦነግ ልሳን ሚዲያ (የኦሮሞ ነጻነት ድምጽ በኦሮምኛ ምእፀሩ/SBO) ሁለት ጋዜጠኞች ናቸው፡፡ገዢውን የብልጽግና ፓርቲን በዚሁ መግለጫው የከሰሰው ኦነግ ትናንት ታህሳስ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. 10 (አስሩም) አባላቶቹ በመንግስት የፀጥታ አካላት ተወስደው ለእስር መዳረጋቸውንም አብራርቷል፡፡የፓርቲው ጊዜያዊ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እርምጃውን ብልጽግና ፓርቲ በኦነግ ላይ የከፈተው ዘመቻ አካል ብለውታል።በገዢው የብልጽግና ፓርቲ በኩል አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ቃል አቀባይ አቶ ታዬ ደንደአ ግን ክሱን በማጣጣል፤ ሂደቱን ገለልተኛ ተቋማት የህግ የበላይነትን ለማስከበር የሚወስዱት እርምጃ ነው ብለውታል፡፡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።
ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW