1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከረዩ አባ ገዳን ጨምሮ የ14 ሰዎች ግድያ ያስከተለው ውዝግብ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 1 2014

ባለፈው ሳምንት በምሥራቅ ሸዋ ቦሰት ወረዳ የከረዩ አባገዳን ጨምሮ በ14 ሰዎች ላይ ለተፈጸመው ግድያ አስተያየታቸውን ለመገናኛ ብዙሃን የሰጡ የአከባቢው ነዋሪዎች እና የተጎጂ ቤተሰቦች የመንግሥት የፀጥታ አካላትን ተጠያቂ ሲያደርጉ፤ መንግሥት በበኩሉ በአከባቢው ይንቀሳቀሳሉ ያላቸውን ታጣቂዎች ወቅሷል።

Karte Äthiopien englisch

«ኢሰመኮ ጉዳዩን አጣራለሁ»

This browser does not support the audio element.

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ምሽት የከረዩ አባገዳ ከድር ሃዋዝ ቦሩ እና ሌሎች 13 ሰዎች ሲገደሉ አብረው ተይዘው የተወሰዱት ከ20 በላይ ሰዎች የት እንደገቡ አለመታወቁ እንዳስጨነቃቸው ቤተሰቦቻቸው ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። የኦሮሞ አባገዳዎች ሕብረት ሰብሳቢ አባገዳ ጂሎ ማንኦ ግድያውን የፈፀመው ማንም ይሁን ማን የሚወገዝ በመሆኑ ሕብረቱ ተሰብስቦ ውሳኔ ለማስተላለፍ ማቀዱን ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት በምሥራቅ ሸዋ ቦሰት ወረዳ የከረዩ አባገዳን ጨምሮ በ14 ሰዎች ላይ ለተፈጸመው ግድያ አስተያየታቸውን ለመገናኛ ብዙሃን የሰጡ የአከባቢው ነዋሪዎች እና የተጎጂ ቤተሰቦች የመንግሥት የፀጥታ አካላትን ተጠያቂ ሲያደርጉ፤ መንግሥት በበኩሉ በአከባቢው ይንቀሳቀሳሉ ያላቸውን ታጣቂዎች ወቅሷል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በርቀት በሰበሰባቸው መረጃዎች እውነታውን ለመደምደም በመቸገሩ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ባለሙያዎቹን ወደ ስፍራው በመላክ ምርመራ ለማድረግ ማቀዱን አሳውቋል።

 ስዩም ጌቱ 

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW