1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከርሰምድር ዉኃ መመናመን ስጋት በምስራቅ ሐረርጌ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 9 2011

ከዓመታት በፊት የአካባቢው ገፀ በረከት የነበረው የሀረማያ ሐይቅ እንደ ዋዛ አንድ ቀን እብስ ብሎ ይጠፋል ያለ ብዙም አልነበረም ፡፡ ከዓመታት በፊት ግን ወደ ላይ ይትነን ወደ ውስጥ ይስረግ ብዙዎች ባልገባቸው መንገድ የሀረማያ ሐይቅ ደረቀ፡፡

Äthiopien Haramaya See
ምስል DW/Mesaye Tekelu

በሀረማያ አካባቢ የሚገኘው የከርሰ ምድረ ውኃ ሐብት ትልቅ ስጋት ተጋርጦበታል

This browser does not support the audio element.


ከዓመታት በፊት የአካባቢው ገፀ በረከት የነበረው የሀረማያ ሐይቅ እንደ ዋዛ አንድ ቀን እብስ ብሎ ይጠፋል ያለ ብዙም አልነበረም ፡፡ ከዓመታት በፊት ግን ወደ ላይ ይትነን ወደ ውስጥ ይስረግ ብዙዎች ባልገባቸው መንገድ የሀረማያ ሐይቅ ደረቀ፡፡ ሀረማያ ሐይቅ ታሪክ ሆነ፡፡ የሀይድሮ ጂኦሎጂስት ባለሙያው ኃይሌ አረፋይኔ በአካባቢው የከርሰ ምድር ውኃ ሀብት ላይ ያደረጉትን ጥናት በሚመለከት ለ«DW» በስልክ እንደገለፁት ካለፈው ታሪክ መማር ያልተቻለ እንደሆን በሀረማያ አካባቢ የሚገኘው የከርሰ ምድረ ውኃ ሐብትም ትልቅ ስጋት ተጋርጦበታል፡፡ በዘርፉ ዓለም አቀፍ የጥናት ማድረጊያ መሳርያዎችንና መስፈርቶችን ተከትሎ ከሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተካሄደ ነው ባሉት ጥናት የተገኘው ውጤት ካመለከተው ግዜ ባነሰም ችግሩ ሊፈጠር እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ነዋሪነታቸውን በአውስትራልያ ያደረጉት እኝህ ባለሞያ ከአመታት በፊት እንደዋዛ ሙሉ በሙሉ በመድረቅ  ከገፀምድር የጠፋው የሀረማያ ሐይቅ  የጠፋበትን ምክንያት ምንነት በጥናት ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል፡፡ የሀይድሮጊኦሎጂስት ባለሞያው አሁን ስጋት የተጋረጠበትን የሀረማያ አካባቢ የከርሰ ምድር ውኃ ሐብት ከጥፋት ለመታደግ በጥናቱ የተመለከቱ መፍትሄዎችን አብራርተዋል ፡፡አጥኚው የዚሁ ሀብት ተጠቃሚ የሆነው የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ጥናቱ እንዲጠና ማድረጉ አንድ እርምጃ መሆኑን ጠቅሰው ለመፍትሄው ሁሉም መረባረብ አለበት ብለዋል፤ በተለይ ውኃ ቆጣቢ ቴክኖሎጂን በስራ ላይ ማዋል ይገባል ነው ያሉት፡፡ የገፀ ምድሩን ሐብት ያጣው የሀረማያ አካባቢ ዛሬ ላይ የከርሰ ምድር ውሀ ሐብቱን ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ የሚያስችለው መፍትሄ በእጁ ስለመሆኑ ጠቁመዋል ፡፡

ምስል DW/Mesaye Tekelu

መሳይ ተክሉ 


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW