የከርሰ ምድር ዉሃ ብክለት
ማክሰኞ፣ ሰኔ 5 2004ማስታወቂያ
የቅመማዉ ሳይንስ የሃይድሮጂን እና የኦክስጅን ዉህደት ዉጤት ነዉ ሲል ይተነትናል ንፁህ ዉሃን። ዉሃ በሠዎችና እንስሳት እንቅስቃሴ እና ተግባራት የመበከል እክል እንደሚገጥመዉ ሁሉ በተፈጥሮም ንፅህናዉን ለጠበቅ መጠናቸዉ የበዛ ንጥረነገሮች በዉስጡ ሲይዝ ብክለት ነዉ።
በቀን ሁለት ሊትር ዉሃ መጠጣት ለጤና መልካም እንደሆነ የሚሰጠዉ ምክር እንዳለ ሆኖ የሚጠጣዉን ዉሃ አስተዉሎ መጠጣቱ ይመከራል። በኢንዱስትሪ በሰለጠነዉ ዓለም ዉሃ ዋነኛ ንግድ እንደመሆኑ ዉስጡ የያዘዉ የንጥረነገር መጠን እየተዘረዘረ፤ በቤተ ሙከራ ገብቶ ጥራቱም እየተፈተሸ ደረጃ ይሰጠዋል። በአዳጊዉ ዓለም ፅድቁ ቀርቶ እንዲሉ ጉሮሮ ማራሻ የሚጠጣዉም ጉልበት ሳያደክም በተገኘ ሊባል ቢችልም፤ የስምጥ ሸለቆ አካባቢ የገፀ ምድርም ሆነ ከርሰ ምድር ዉሃ ትኩረትን ይሻል። ዉሃ የቅንጦት ሸቀጥ አይደለምና። የተፈጥሮ ክስተት እሳተ ጎመራ ያስከተለዉ ብክለት ሳያንስ ሰዉሰራሹ ብክለት መፍትሄ ይሻል።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ