1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከተራ በዓል በአዳማ ከተማ

ዓርብ፣ ጥር 10 2016

ዛሬ ከሰኣት 8፡00 ገደማ ከየአድባራቱ የወጡትን ታቦታት በርካታ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን አጅበውአቸው ወደየታቦታት ማደሪያ ስሸኙም ነበር፡፡ የወጣቶች ዝማሬ እና የካህናቱ ህብረዜማ ከየታቦታቱ ጎን ደምቆም ይስተዋላል፡፡

በዓሉ በድምቀት ከተከበረባቸዉ ከተሞች አንዱ አዳማ (ናዝሬት)
2016 የከተራ በዓል አከባበር በአዳማ (ናዝሬት) ከተማ ምስል Seyoum Getu/DW

የከተራ በዓል በአደማ ከተማ

This browser does not support the audio element.

 

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ውስጥ በምትገኘውበአዳማ (የቀድሞዋ ናዝሬት) ከተማም የከተራ በዓል  በደማቅ መንፈሳዊ ሥርዓት ተከብሮ ውሏል፡፡ከከተማዋ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተጓዙ ታቦታት የሚገናኙበት የመስቀል አደባባይ የበዓሉ ዋነኛ ማዕከል ሆኖ ዉሏል።

በአዳማ ከተማ ዛሬ ከሰኣቱን የከተራ በዓል በደማቅ ስነስርዓት ተካሂዶ ውሏል፡፡ ዛሬ ከሰኣት 8፡00 ገደማ ከየአድባራቱ የወጡትን ታቦታት በርካታ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን አጅበውአቸው ወደየታቦታት ማደሪያ ስሸኙም ነበር፡፡ የወጣቶች ዝማሬ እና የካህናቱ ህብረዜማ ከየታቦታቱ ጎን ደምቆም ይስተዋላል፡፡

የበዓሉ ሃይማኖታዊ ትርጓሜ

በአዳማ ከተማ ሶስት የባህረጥምቀት ስርዓት መከወኛ ስፍራዎች ስኖሩት በዋናነት ግን የ21 ታቦታት እና አድባራት ማደሪያ የሆነው መስቀል አደባባይ ወይም የጥምቀት ስፍራ በእጅጉ ይደምቃል፡፡ ዶይቼ ቬለ ዛሬ የጥምቀት በዓል ዋዜማ የሆነው የከተራ በዓልን በስፍራው በጎበኘበት ወቅት ስለ እለቱ ትርጓሜ እና የበዓሉን አከባበር በተመለከተ የምስራቅ ሸዋአገረስብከት ምክትል ስራ አስከያጅ ሊቀካህናት ነጋሽ ሃብተወልድን አነጋግሮአቸዋል፡፡

የዘንድሮዉ (2016) የከተራ በዓል በአዳማ (ናዝሬት) ከተማ በድምቀት ተከብሯልምስል Seyoum Getu/DW

“የከተራ በዓል ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዮሓንስ ለመጠመቅ የሄደበትን ለማስታወስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትር 10 ቀን ስርዓቱን በያመቱ ታስታውሳለች” ብለዋል፡፡ ታቦታቱ ከማደራቸው ተነስተው ወደ ባህረ ጥምቀት በመጓዝ በሚከበረው በዚህ የአደባባይ በኣል እለት በአዳማ ከተማ በዋናነት ስርዓተ ጥምቀቱ በሚከበርበት መስቀል አደባባይ 21 ታቦታት እንደሚያድሩም አስረድተውናል፡፡

የበዓሉ ታዳሚያን አስተያየት

በበዓሉ አከባበር ላይ እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ ታድመዋል፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የበዓሉ ታዳሚያንም በጉጉት የሚጠበቅ ያሉትን ዓመታዊውን የከተራ እና ጥምቀት በዓልን በያመቱ በዚሁ ስፍራ በህብረት ወጥተው እንደሚያከብሩ ያስረዳሉ፡፡

በአዳማ (ናዝሬት) ከተማ የከተራ በዓል ከተከበረባቸዉ አካባቢዎች አንዱምስል Seyoum Getu/DW

በዚህ የበዓሉ አከባበር ላይ በርካታ ወጣቶችን የዘንባባ ዛፍ ቅጠል አስይዘው ከታቦታቱ ፊት ቀደም ብለው በመጓዝ የምስጋና ቃል የሚያሰሙ እድሜያቸው ጠና ያለ አባት ግን የበርካቶችን ትኩረት ይስባሉ፡፡ ንጉሴ መሸሻ የተባሉ እኚህ  አባት የዘንባባ ዛፉን ይዘው ለከተራ በዓል የወጡትም ለሰላም አንድነቱ ጥሪ ለማቅረብ ነው ሲሉ ሃሳባቸውን አጋርተውናል፡፡ “ሰላም ከሌለ ሁሉም ከንቱ ነው፡፡ ከጦርነት፣ ከርሃብ ከእርዛት እግዝአብሔር ይተብቀን” ሲሉም አስተያየታቸውን አክለዋል፡፡

ሥዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW