1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኩላሊት ንቅለ ተከላ

ሰኞ፣ መስከረም 22 2010

የማዕከሉ ሃላፊዎች በዚህ ሳምንት ማዕከሉን ለጎበኙ ጋዜጠኖች እንደተናገሩት ህክምናውን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ለማካሄድ በኩላሊት ንቅለ-ተከላ የሚሰማሩ ሐኪሞች በሀገር ውስጥ እየሰለጠኑ ነው።

Äthiopien Addis Abeba Nieren-Transplantation
ምስል፦ DW/Getachew Tedla

የኩላሊት ነቀላ እና ተከላ

This browser does not support the audio element.

በአዲስ አበባው የጳውሎስ ሆስፒታል የሚገኘው የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማዕከል ህክምናውን በቅርቡ ያለምንም የውጭ እርዳታ ማካሄድ የሚችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን አስታወቀ። የማዕከሉ ሃላፊዎች በዚህ ሳምንት ማዕከሉን ለጎበኙ ጋዜጠኖች እንደተናገሩት ህክምናውን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ለማካሄድ በኩላሊት ንቅለ-ተከላ የሚሰማሩ ሐኪሞች በሀገር ውስጥ እየሰለጠኑ ነው። ከረዥም ጊዜ ጥረት በኋላ በኢትዮጵያ መሰጠት የጀመረው ይህ ህክምና በዓይነቱ ልዩ መሆኑንንም ሃላፊዎቹ ተናግረዋል። ማዕከሉን የጎበኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ቀጣዩን ዘገባ አዘጋጅቷል። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW