1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኪር እና የማቻር ውይይት

ሐሙስ፣ ሰኔ 14 2010

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች አዲስ አበባ  በሚያካሂዱት ድርድር ላይ የተሳተፈው የደቡብ ሱዳን አማጺ ቡድን በኃይል የሚጫን የሰላም ሃሳብን እንደማይቀበል አስታወቀ። ቡድኑ ባወጣው መግለጫ  ጊዜ እንዲሰጠውም መጠየቁ ተዘግቧል።

Südsudan Rebellenführer Riek Machar in Juba
ምስል፦ Reuters/Stringer

የኪር እና የማቻር ንግግር

This browser does not support the audio element.

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች አዲስ አበባ  በሚያካሂዱት ድርድር ላይ የተሳተፈው የደቡብ ሱዳን አማጺ ቡድን በኃይል የሚጫን የሰላም ሃሳብን እንደማይቀበል አስታወቀ። ቡድኑ ባወጣው መግለጫ  ጊዜ እንዲሰጠውም መጠየቁ ተዘግቧል። የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና የአማጽያኑ መሪ ሪየክ ማቻር ትናንት ማታ አዲስ አበባ ውስጥ ባካሄዱት የፊት ለፊት ውይይት ላይ ሁለቱ ወገኖች ስለሀገሪቱ የሰላም ተስፋ በስፋት መነጋገራቸውን መግለጫው አስታውቋል። ኪር እና ማቻር አዲስ አበባ እንዲነጋገሩ የጋበዟቸው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ በድርድሩ ላይ መገኘታቸውን አሶስየትድ ፕሬስ ዘግቧል። የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ኢጋድ ሁለቱን ወገኖች ለማስማማት ከዚህ ቀደም ያካሄዳቸው ጥረቶች አልተሳኩም። ሁለት ዓመት ከሚጠጋ ጊዜ በኋላ ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ  የተካሄደው የፊት ለፊት ውይይት በስምምነት ይጠናቀቃል የሚል ተስፋ ነበረ።  

 

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW