1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካምፓላው ፍንዳታና የአፍሪካ ቀንድ ቀውስ

ሰኞ፣ ሐምሌ 12 2002

የቦምብ ጥቃቱ በሶማሊያ ዙሪያ ሃገራት የሚከተሉትን ፖሊሲ ሊያስቀይር እንደሚችል የፖለቲካው ተንታኞች ይናገራሉ።

በጥቃቱ የመቁሰል አደጋ የደረሰበት አሜሪካዊምስል picture-alliance/dpa

19ኛው የዓለም ዋንጫ በተለይ የፍጻሜው የስፔይንና የኔዘርላንድ ጨዋታ ዓለምን ከዳር እስከዳር በአንድ ስሜት ውስጥ ከቷል። ዓይንና ጆሮ ከቴሌቪዥን መስኮት ላይ ተተክሏል። እሁድ ምሽት ሐምሌ 4/2002 ከጆሀንስበርግ ርቃ የምትገኘው ካምፓላ የዓለም ህዝብ እየታደመ ያለውን የፍጻሜ ጨዋታ አልተነፈገችም። እንደሁሉም በቴሌቪዥን መስኮት ጨዋታውን መከታተል ጀመረች። እንደሁሉም ግን የዳኛው የመጨረሻው የፊሽካ ድምጽ እስኪሰማ አልጠበቀችም። ቦምብ አናወጣት። በአንድ ጊዜ ግን በሁለት ቦታዎች።

በኡጋንዳ መዲና ካምፓላ የደረሰው የቦምብ ጥቃት በየአቅጣጫው እያነጋገረ ነው። 76 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈበት ይኸው ፍንዳታ ብዙ ነገሮችን መዟል። ብዙ ነገሮችንም ተብትቧል። ብዙ ሀገራትን አስደንግጧል። አስቆጥቷል። በተለይ አልሸባብ ለጥቃቱ ሃላፊነቱን መውሰዱ የቀጠናውን ወዴትነት ግራ አጋብቷል። የካምፓላው ፍንዳታ የፈጠረው የሀዘን ቆፈን ሳይለቅ ካምፓላ የአፍሪካ ህብረትን ስብሰባ እያስተናገደች ነው።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW