1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማክሰኞ፣ ኅዳር 27 2009

የትግራይ ክልል ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክርቤት ትላንትና ባካሄደዉ አስቸኳይ ጉባኤ አዳዲስ የካብኔ አባላትን ለተለያዩ የመንግስት የሃላፊነት ደረጃ ሾሟል። 

Äthiopien 40. Jahrestag TPLF
ምስል DW/T. Weldeyes

mmt Tigray Cabinet Appoint. - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

 

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በአቶ አባይ ወልዱ ያቀረቡዋቸውን አዲሶቹን ተሿሚዎች የክልሉ ምክር ቤት አፀድቆታል።

አዲሱ ካቢኔ 12 አባላት አሉት።

እንደሚታወሰው፣ ከጥቂት ጊዜ በፊት በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ በፌዴራል መንግሥቱ እና ሁከት በታየባቸው ሁለቱ ክልሎች  ሹምሽር ተካሂዶዋል።

ለትግራይ የእርሻና ገጠር ልማት ቢሮ ሃላፊነት የተሾሙት በግብርና ልማት አከባቢ ያተኮረ የ15 ዓመት የከፍተኛ ትምህርት ምርምር ዓለም ተሞክሮ ያላቸው ዶክተር አትንኩት መዝገቡ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት፣ የአዳዲሶቹ የካቢኔ አባላት  ሹመት ትልቅ ለዉጥ ስለሆነ ለህዝብ ትልቅ ጠቀሜታ አለው።

ይህ የካብኔት ሽምሽሩ አዎንታዊ ቢሆንም «ወሳኝ የሚባሉ የህወሃት ባለስልጣናት ስላልተነኩ» ብዙም «ለዉጥ አያመጡም» ሲሉ የዓረና ትግራይ ለድሞክራስና ለሉኣላዊነት ፓርቲ የስራ ኣስፈፃሚ ኣመራር አባል የሆኑት አቶ አብርሃ ደስታ ለዶቼቬለ ገልጸዋል።

በፌስቡክ ደህረ ገፃችን ላይ ሹምሽሩን በተመለከተ አወያይተን ነበረ። አስተያየታቸዉን ከሰጡንም ዉስጥ «ተሾሙም ተሰናበቱም የነሱ ጉዳይ ነው እኛን አይወክልም» ያሉ ሲኖሩ፣ ሌሎች ደግሞ «ለውጥ ያመጣሉ ብለን እንጠብቃለን» በሚል አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።

መርጋ ዮናስ

አረያም ተክሌ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW