1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካንሰር ህክምና ማዕከል በሀረር ከተማ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 8 2016

በሀረማያ ዩንቨርስቲ ሕይወት ፋና ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የካንሰር ህክምና ማዕከል በቅርቡ የጀመረው የጨረር ህክምና አገልግሎት በርካቶችን ከእንግልት እና ወጪ መታደጉን ተገልጋዮች ገለፁ። ማዕከሉ የጨረር ህክምና አገልግሎቱ መሰጠት በጀመረባቸው ያለፉት አራት ወራት ውስጥ አምስት መቶ ሰዎች አገልግሎት ማግኘታቸው ተገልጿል ።

በሀረማያ ዩንቨርስቲ ሕይወት ፋና ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የካንሰር ህክምና ማዕከል
በሀረማያ ዩንቨርስቲ ሕይወት ፋና ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የካንሰር ህክምና ማዕከል ባለፉት አራት ወራት ውስጥ አምስት መቶ ሰዎች አገልግሎት ማግኘታቸውን እና ስምንት ሺህ አዲስ ህክምና ፈላጊዎች መመዝገባቸውን ዐስታውቋል።ምስል Messay Teklu/DW

ባለፉት 4 ወራት ውስጥ 500 ሰዎች አገልግሎት አግኝተዋል

This browser does not support the audio element.

በሀረማያ ዩንቨርስቲ ሕይወት ፋና ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የካንሰር ህክምና ማዕከል በቅርቡ የጀመረው የጨረር ህክምና አገልግሎት በርካቶችን ከእንግልት እና ወጪ መታደጉን ተገልጋዮች ገለፁ። ማዕከሉ የጨረር ህክምና አገልግሎቱ መሰጠት በጀመረባቸው ያለፉት አራት ወራት ውስጥ አምስት መቶ ሰዎች አገልግሎት ማግኘታቸውን እና ስምንት ሺህ አዲስ ህክምና ፈላጊዎች መመዝገባቸውን ዐስታውቋል።

በሀገሪቱ ከሚገኙ ሦስት የካንሰር ህክምና ማዕከላት አንዱ በመሆን ከአንድ ዓመት በፊት ወደ ስራ የገባው እና በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ሆስፒታል የሚገኘው የካንሰር ህክምና ማዕከል በወቅቱ የጨረር ህክምና ባለመጀመሩ ወደ ጅማ ሊላኩ እንደነበር የሚናገሩት የድሬደዋ ነዋሪዋ ወ/ሮ ክቡ በዚያው ጊዜ መጀመሩ ጭንቀታቸውን እንዳስቀረ ገልፀዋል ።

ሌላኛው የሀረር ከተማ ነዋሪ እና የማዕከሉ አገልግሎት ተጠቃሚ ማዕከሉ በተሟላ አገልግሎት በአካባቢው ሥራ መጀመር እንግልት ከማስቀረት ባለፈ አገልግሎቱም ጥሩ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

የማዕከሉን አገልግሎቱን የተሟላ የሚያደርገውን ለካንሰር ህመም የሚሰጥ የጨረር ህክምና ለመጀመር ዝግጅቱን ጨርሶ ከአራት ወራት በፊት አገልግሎቱን  መስጠት ጀምሯል የሚሉት የማዕከሉ ዳይሬክቶሬት ዶ/ር አብዲ አሚን በጥቂት ጊዝያት በቁጥር በርካታ አገልግሎት መስጠቱን ከዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ማዕከሉ ከሀገሪቱ ዜጎች በተጨማሪ ከሀጎራባች ሀገራት ለሚመጡ ሰዎች እያገለገለ ያለ የምስራቅ ኢትዮጵያ ህክምና ማዕከል መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር አብዲ አንድ ተጨማሪ መሳሪያ ቢኖር የተሻለ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት በተከናወነ መርሀ ግብር በክብር ዶክተር አሊ ቢራ ስም የተሰየመውን ይህን ማዕከል የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ የሀረማያ ዩኒቨርስቲ እና የሀረሪ ክልል ዐስታውቀዋል ። 

መሳይ ተክሉ

ማንተጋፍቶትስለሺ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW