1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኬንያ አትሌቶች በበርሊን ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች አሸነፉ

እሑድ፣ መስከረም 11 2018

በወንዶች የ29 አመቱ ስባስቲያን ሳዌ ያሸነፈ ሲሆን፤ ይህ ውጤት በለንደን ማራቶን ካሸነፈ ከአምስት ወራት በኋላ የተመዘገበ መሆኑ ነው።በሴቶችም ሌኛዋ የሀገሩ ልጅ ሮዝሜሪ ዋንጂሩ ፉክክሩን በአንደኛነት ጨርሳለች።ባለፈው አመት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን በወንዶች ሚልኬሳ ​​መንገሻ፤ በሴቶች ትግስት ከተማ ለኢትዮጵያ ድርብ ድል አስገኝተው ነበር።

Deutschland Berlin 2025 | Läufer beim Start des BMW Berlin Marathon
ምስል፦ Gabriel Kuchta/Getty Images


ከ55,000  በላይ ሯጮች ተሳተፈውበታል በተባለው በዛሬው የበርሊን ማራቶን  በወንዶችም በሴቶችም የኬንያ አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል።
በወንዶች  የ29 አመቱ ሰባስቲያን ሳዌ 2፡02፡15 በሆነ ሰአት ያሸነፈ ሲሆን፤ ይህ ውጤት በለንደን ማራቶን ካሸነፈ ከአምስት ወራት በኋላ የተመዘገበ መሆኑ ነው።በሴቶችም ሌኛዋ የሀገሩ ልጅ ሮዝሜሪ ዋንጂሩ 2፡21፡05 በሆነ ሰአት ፉክክሩን በአንደኛነት ጨርሳለች።በሴቶች ደራ ዲዳ  እና  አዝመራ ገብሩ  ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል።

በርሊን ፈጣን የማራቶን መስመር የሚል ስም የነበራት ቢሆንም ሁለቱም  ኬንያውያውያን አትሌቶች የዛሬውን ውድድር ያጠናቀቁበት ስዓት  ከአለም ክብረወሰን  በጣም የራቀ ነበር።ስባስቲያን ሳዌ ከዓለም ክብረወሰን 1 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ ዘግይቶ  የገባ ሲሆን ፤ሮዝመሪ ዋንጅሩ ደግሞ 11 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ ዘግይታ ገብታለች።ለዚህም በጀርመን መዲና በርሊን  የነበረው ከወትሮው የተለየ እርጥበታማ የበጋ ወቅት ሊሆን ይችላል ተብሏል።

በዘንድሮው የበርሊን ማራቶን በወንዶች የ29 አመቱ ኬንያዊው አትሌት ሰባስቲያን ሳዌ አሸንፏል።ምስል፦ Tobias Schwarz/AFP/Getty Images

ባለፈው አመት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን በወንዶችሚልኬሳ ​​መንገሻ (2፡03፡17)  በሴቶች ትግስት ከተማ  (2፡16፡42)ለኢትዮጵያ ድርብ ድል  አስገኝተው ነበር።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው 20ኛው  የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት የብር እና ሁለት የነሀስ  በድምሩ አራት ሜዳሊያዎችን በማግኘት በ20ኛ ደረጃ አጠናቃለች።ከመስከረም 3 ቀን 2018 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው እና 200 ገደማ ሀገራት የተሳተፉበት ውድድር ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል።በውድድሩ ከ2000 በላይ አትሌቶች በ49 የውድድር አይነቶች ተሳትፈዋል።  

 

ፀሀይ ጫኔ

ዮሀንስ ገብረእግዚአብሄር

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW