1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኬንያ ጦር፥ «አሚሶም»ና ሶማሊያ

ዓርብ፣ መጋቢት 21 2004

የዛሬ ስድስት ዓመት ግድም የአፍሪቃ ሕብረት፥ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ወደ ሶማሊያ ለማዝመት ሲወስን የሶማሊያ ጉዳይ ባንድ ወይም በሌላ መልኩ የሚነካካቸዉ እንደ ኢትዮጵያ፥ ኬንያና ጅቡቲን የመሳሰሉ ሐገራት ሠራዊት እንዳያዘምቱ ተወስኖ ነበር።ዛሬ ግን

NUR ZUR REDAKTIONELLEN NUTZUNG! A handout picture provided by the African Union-United Nations Information Support Team shows a Ugandan soldier serving with the African Union Mission in Somalia (AMISOM) standing at the back of an amoured fighting vehicle near a defensive position along the front-line in the Yaaqshiid District of northern Mogadishu, Somalia, 05 December 2011. In the face of a surge of car bombings and improvised explosive device (IED) attacks, the 9,700-strong African Union force continues to conduct security and counter-IED operations in and around the Somali capital. EPA/STUART PRICE / AU-UN IST PHOTO / HANDOUT HANDOUT EDITORIAL USE ONLY/NO SALES +++(c) dpa - Bildfunk+++ dpa 28561906
የአፍሪቃ ሕብረት ጦርምስል picture-alliance/dpa

30 03 12


የሶማሊያን ገሚስ ደቡባዊ ግዛት የሚቆጣጠረዉ የኬንያ ጦር በሶማሊያ የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት (AMISOM)ን ዛሬ በይፋ ተቀላቀለ።የኬንያ ጦር አዛዦች እንዳስታወቁት ሶማሊያ የሚገኘዉ ጦራቸዉ ከእንግዲሕ የሚታዘዘዉ በአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት ዕዝ ነዉ።ይሁንና በኬንያና በአሚሶም መካካል በተደረገዉ ሥምምነት መሠረት የኬንያ ጦር ካለፈዉ ጥቅምት ጀምሮ የሠፈረበትን የደቡባዊ ሶማሊያ ግዛትን ለቅቆ ወደ ሌላ አካባቢ አይዘምትም።AMISOMን የተቀላቀለዉ የኬንያ ጦር ከ4 ሺ በላይ አባላት አሉት።የዓለም አቀፍ የሥልታዊ ጥናት ተቋም (ISS) ከፍተኛ አጥኚ አንድሬዉስ አሳ-አሳሞሐ እንደሚሉት የኬንያ ጦር የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊትን ቢቀላቀልም የኬንያ መሠረታዊ አላማ አልተለወጠም።አሳ-አሳሞሐን ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል።


ሶማሊያ የሠፈረዉ የኬንያ ጦር የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት (AMISOM)ን እንዲቀየጥ ዉይይት ድርድሩ ከተጀመረ ቆይቷል።እስካሁን አላግባባ ያለዉ ከማዕከላዊ ሶማሊያ ብዙ ርቆ ኬንያ ጥግ ታኛቸዉ ጁባ የሠፈረዉ የኬንያ ጦርን ሞቃዲሾ ከሚገኘዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጠቅላይ ዕዝ ጋር ማቀናጀቱ ነበር።

አሁን ግን ISS በሚል የእስግሊዝኛ ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ አጥኚ ተቋም ባልደረባ አንድሬዉስ አሳ-አሳሞሐ እንደሚሉት የኬንያና እስካሁን ዩጋንዳንና ብሩንዲን ወታደሮች ብቻ የሚያስተናብረዉ እና በዩጋንዳ የሚታዘዘዉ የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት አዛዦችን አላግባባ ያለዉ ሐሳብ ተወግዷል።

የኬንያና የዩጋንዳ ወታደራዊ ሹማምንት ባደረጉት ስምምነት መሠረት የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት ሰወስት ቀጣናዎች ይኖሩታል።የመጀመሪያዉ እስካሁን ያለዉ የመቃዲሾዉ ነዉ።ሁለተኛዉ ለኬንያ፥ ተሰጠ።ሰወስተኛዉ ደግሞ ለሌላ ሐገር (ምናልባት ከዘመተ ለጅቡቲ ሠራዊት) የተቀመጠ ነዉ።

«ኬንያ ቀጣና ሁለት ላይ ናት።እና ወታደሮቿ፥ እንዳልከዉ፥ በሚያዋስናት የጁባ ክፍለ-ግዛት ይንቀሳቀሳሉ።ጠቅላይ አዛዡ ግን አሁን እንዳለዉ ይቀጥላል።ኬንያዎች ሥፍራ እንዲያገኙ ሽግሽግ ይደረጋል።የአጠቃላይ ተልዕኮዉን የቃል አቀባይነትና የመረጃ ክፍል ሐላፊነት ሥልጣንን ኬንያዎች ይይዙታል።»

ኬንያ ዉስጥ የተጣለ አደጋን በጣሙን የቅድሞ የኬንያ ቅኝ ገዢ የብሪታንያ አገር-ጎብኚ ዜጎች ኬንያ ዉስጥ መገደል-መታገታቸዉን ለመቀበል ደቡባዊ ሶማሊያ የዘመተዉ የኬንያ ጦር አለማ ያኔ እንደተባለዉ ለእገታ-ግድያዉ ተጠያቂ የተደረገዉን አሸባብን ከኬንያ አዋሳኝ ድንበር ማጥፋት ነበር።

የኬንያን ጦር ሊንዳኢንቺ ባለዉ ዘመቻዉ አሸባብን ለማጥፋት ኪስማዩን የመሳሰሉ የአሸባብ ጠንካራ ይዞታዎችን ባጭር ጊዜ እንደሚቆጣጠር አዛዦቹ አስታዉቀዉ ነበር።የኬንያ ጦር ዛሬ በስድስተኛ ወሩAMISOMን ሲቀየጥ የጥቅምቱ ዛቻ-ፉከራ ቢያንስ ገሚሱ ገቢር አልሆነም።ኪስማዩም አሸባብ እጅ ናት።አሳ-አሳሞሐ ግን ዘመቻ ሊንዳኢንቺ ዉል አልሳተም ባይ ናቸዉ።

«እንደሚመስለኝ ከዚሕ ትንሽ ለየት ይላል።የኬንያ ጦር አላማ አልታጎለም።ይሕን የምልበት ምክንያት ያስገኙትን ዉጤት ብትመለከት፥ በመጀመሪያ ደረጃ የዘመቻ ሊንዳኢንቺ መሠረታዊ አለማ የአሸባብንና የሌሎች ተዋጊ ሐይላት አባላትን ከኬንያ ድንበር መግፋት ነዉ።እና ኬንያን በሚያዋስነዉ የሶማሊያ ግዛት አንድ መቶ ኪሎ ሜትር የሚደርስ ከሌላ ጦር እንቅስቃሴ እግድ ቀጣና መመስረት ነዉ።ይሕን መሠረታዊ አላማ ካየን የኬንያ ጦር ተልዕኮ አልተሳካለትም ብሎ የሚከራከር የለም።ከዚሕም በተጨማሪ ዉስብስቡ የሽምቅ ዉጊያ ተልዕኮዉን እኛ ይሆናል ብለን ከምናስበዉ በላይ ከባድ አድርጎታል።»

ይሑንና አሸባብ፥ የኬንያ ጦር ሊያጠፋዉ ከዛተ-ከዘመተበት ጥቅምት ከብዙ አመታት በፊት ሽምቅ ተዋጊነቱን የማያዋቅ-ከነበረ ሶማሊያን የማያዉቅ ነዉ።ብቻ የኬንያ ጦር AMISOMን ቢቀላቀልም ደቡባዊ ሶማሊያን እንደ መተማመኛ ቀጣና መቆጣጠሩን ይቀጥላል።

«ደሕና ኬንያ የምትገፋዉን (ሐሳብ) እና ከመሪዎቿ የሚነገረዉን ካጤንነዉ የኬንያ ወታደሮች ከእንግዲሕ የሚታዘዙት በአሚሶም ስር ቢሆንም፥ የሚንቀሳቀሱት በነዚያ መስመሮች አካባቢዎች ነዉ።ድንበራቸዉ አጠገብ።ሥለዚሕ ጥብቅ ቀጣና የመመስረቱ መሠረታዊ አላማ አሁንም አለ።»

የዛሬ ስድስት ዓመት ግድም መጀመሪያ ኢጋድ፥ በማከታተል የአፍሪቃ ሕብረት፥ የአፍሪቃ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ወደ ሶማሊያ ለማዝመት ሲወስኑ የሶማሊያ ጉዳይ ባንድ ወይም በሌላ መልኩ የሚነካካቸዉ እንደ ኢትዮጵያ፥ ኬንያና ጅቡቲን የመሳሰሉ ሐገራት ሠራዊት እንዳያዘምቱ ተወስኖ ነበር።ዛሬ ግን ያቀርቶ አይነት ነዉ-ለሶማሊያ የሚወሰንላት።

ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ

የአ-ሸባብ ሚሊሺያምስል picture-alliance/dpa
የኬንያ ጦርምስል AP
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW