1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኮሌራ መከላከያ ክትባት በደቡብ ኢትዮጵያ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 23 2013

በደቡብ ክልል የኮሌራ ወረርሽኝ ስጋት ላጠላባቸው ግማሽ ሚሊዮን ነዋሪዎች የክትባት አገልግሎት በመሰጠት ላይ ነው። ክትባቱ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ሦስት ዞኖች በሚገኙ 13 ወረዳዎች ውስጥ እየተሰጠ እንደሚገኝ የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዪት አመልክቷል።

Äthiopien Stadtansicht Awassa
ምስል፦ DW/S. Wegayehu

«በሦስት ዞኖች በ13 ወረዳዎች እየተሰጠ ነው»

This browser does not support the audio element.

በደቡብ ክልል የኮሌራ ወረርሽኝ ስጋት ላጠላባቸው ግማሽ ሚሊዮን ነዋሪዎች የክትባት አገልግሎት በመሰጠት ላይ ነው። በደቡብ ክልል ከያዝነው የታኅሣሥ ወር አጋማሽ ጀምሮ በተቀሰቀሰው የኮሌራ ወረርሽኝ 12 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ ከ400 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በበሽታው መታመማቸው ተሰምቷል። የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ ለዶቼ ቬለ (DW) እንደገለጹት ክትባቱ በክልሉ ሦስት ዞኖች በሚገኙ 13 ወረዳዎች ውስጥ እየተሰጠ ይገኛል።

ሸዋንግዛው ወጋየሁ 

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW