1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ«ኮምፓክት ዊዝ አፍሪቃ »የአንድ ዓመት ጉዞ 

ሰኞ፣ ጥቅምት 19 2011

በመጭዉ ማክሰኞ አስራ ሁለት የአፍሪቃ ሀገራት መሪዎች በጀርመን በርሊን ይሰበሰባሉ።መሪዎቹ  ባለፈዉ ዓመት ጀርመን በጀመረችዉና አፍሪካን በኢኮኖሚ ለማጠናከር ባለመዉ »ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ» በተባለዉ «ኢንሸቲቭ»  ላይ ከመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርከል ጋር  በዋናነት ይመክራሉ።

Ghana G20 Compact summit
ምስል DW/I. Kaledzi

compact MMT - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

ይሁን እንጅ የመሪዎቹን ዉይይት አንድን የታወቀ ተዉኔት ደግሞ እንደመጫወት  የሚያዩት አሉ።ለምን ቢባል ተሰብሳቢዎቹ መልዕክቱ  ሁሉም ነገር ተመሳሳይና የታወቀ ነዉ ይሉታል።ጀርመን ያለፈዉ ዓመት የጋናዉን ፕሬዝዳንት ናኖ አኮፎ አዶንና የሩዋንዳዉን ፕሬዝዳንት ፓዉል ካጋሜን በክብር እንግድነት ጋብዛ ታላቅ የአፊሪቃ ጉባኤ አዘጋጅታ ነበር።ርዕሰ ጉዳዮቹ ተደጋጋሚ ናቸዉ። የአዉሮፓና የአፍሪቃን የኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከር፣የአፍሪቃ ብልፅግና ኢንዲጨምር ማድረግ ፣የስደተኞችን ቁጥር መቀነስና ከዚያም የጀርመንን ኢኮኖሚ አትራፊ ማድረግ የሚሉት ናቸዉ።አፍሪቃን ጥሩ የገበያ አጋር ማድረግም ሌላዉ ዓላማ መሆኑን በቅርቡ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርከል ከተናገሩት መረዳት ይቻላል።
»በአፍሪቃ ብዙ ግጭቶች አሉ ።ሰወች በአስቸጋሪ ሁኔታም ቢሆን ይሰደዳሉ። በሌላ በኩል ግን የአፍሪቃ ሀገሮች ለጀርመን ኢኮኖሚ ጥሩ የወደፊት ገበያ ሊሆኑ እንደሚችሉ እናዉቃለን። በዚህ ጉዳይ ሌሎች ሀገሮች ከፍተኛ እንቅስቃሴ አላቸዉ።የአፍሪቃ ሀገራት በየዓመቱ በአማካኝ ጥሩ እድገት እያስመዘገቡ ነዉ። በዓመት አምስት ከመቶና ከዚያ በላይ የኢኮኖሚ ጥንካሬያቸዉ እያደገ ነዉ።ይህ ደግሞ ምርቷን ወደ ዉጭ ለምትልከዉ ጀርመን ጥሩ የወደፊት ገበያ ሊሆን ይችላል።»
11 የአፍሪቃ ሀገራት የታቀፉበት «ኮምፓክት አፍሪካ»ያለፈዉ ዓመት በታላቅ ተስፋ በጀርመን ይፋ ሲደረግ ፤የአፍሪቃን ኢኮኖሚያዊ   ለማጠናከር  ታምራዊ መፍትሄ ተደርጎ ተወስዶ ነበር።ይህ «ኢንሺትቭ »  ሲጀመር የዉጭና የሀር ዉስጥ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል በሚል በአፍሪቃም ቢሆን የተወሰነ ተስፋ ፈጥሮ ነበር።ያም ሆኖ ግን ይህ ስሜት ብዙ አልዘለቀም።  የጀርመን አፍሪቃ ፋዉንዴሽን ዋና ፀሀፊ አንጎ ባዶሬክ እንደሚሉት  ይህ ዉጤት ለአመታት የሚዘልቅ ረጅም ሂደት የመሆኑን ዕዉነታ  መጋፈጥን ይጠይቃል።ባዶሬክ እንደሚሉት «ኮምፓክት» የተሳታፊ ሀገራትን በርትቶ መስራትንም  ይፈልጋል።ከዚህ ጋር በተያያዘም ሀገራቱ ባለሀብቶችን ለመሳብ የሚያስችሉ ፣የዋጋ ግሽበትን መቀነስ ፣የመሰረተ ልማትን ማስፋፋትና አመቺ ያልሆኑ ህጎችን መቀየርየመሳሰሉ 101 ግቦችን ነድፈዋል።
የጀርመን የፋይናንስ ሚንስቴር በበኩላቸዉ ይህ ዕቅድ ከተጀመረ ወዲህ በብዙ ሀገራት ጠቃሚ መሻሻሎች ቢታዩም ብዙ መሰራት ያለባቸዉ ነገሮች መኖራቸዉን ነዉ የገለፁት። እንደ ሚንስትሩ የጀርመን መንግስትና አጋሮቹ ለሀገራቱ የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ እያደረጉ ሲሆን እስካሁን የዉጭ ባለሀብቶች 243 ቢሊዮን ዩሮ የሚጠጋ ገንዘብ አፍስሰዋል።ያም ሆኖ ግን በ 2030 ሀገራቱ መብራትና ዉሃ ለሁሉም ለማዳረስ ብቻ 537 ቢሊዮን ዩሮ እንደሚያስፈልግ ነዉ ጥናቶች የሚያሳዩት። የጀርመን መንግስት በአፍሪቃ መዋዕለንዋይ ለሚያፈሱ ኩባንያዎች ሁኔታዎችን እያመቻቸ ነዉ።ያለፈዉ ነሀሴ ወርም መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርከል ትልልቅ የንግድ ልዑካንን አካተዉ ሴኔጋልና ጋና ተጉዘዉ ነበር።ቢሆንም ግን ነገሮች የታሰበዉን ያህል በፍጥነት እየሄዱ አይደለም። ከአፍሪቃ ጋር ቀደም ሲል ቁርኝት ካላቸዉቦሽን፣ቮልስ ቫገንና አሊያንስን ከመሳሰሉ ኩባንያዎች ዉጭ ሌሎችን መሳብ አልተቻለም።የጀርመን አፍሪቃ ፋዉንዴሽን ዋና ፀሀፊ ኢንጎ በዶሬክ  መፍትሄዉ ሌሎችን የአፍሪቃ ሀገራት በማዕቀፉ ማካተት  ነዉ ይላሉ።
»ኮምፓክት» በተባለዉ ማዕቀፍ ዉስጥ ያሉ ሀገራት፤ በተለይም ቤኒን ፣ ጋናና ሩዋንዳን የመሳሰሉ ከስሃራ በታች ያሉ የአፍሪቃ ሀገራት ለጀርመን ኢኮኖሚ ትልቅ ጠቀሜታ ያላቸዉ አይደሉም። ለአፍሪቃ አካባቢያዊ ኢኮኖሚም ቢሆን እንደዚያዉ። ስለዚህ «ኮምፓክት« እንዲህ አይነቱን ቁርኝት የሚቀጥል ከሆነ ለኢኮኖሚ ወሳኝ የሆኑ ሀገሮችን ማለትም ከምስራቅ አፍሪቃ ኬንያን፤ከምዕራብ አፍሪቃ ደግሞ ናይጄሪያን የመሳሰሉ ሀገሮች ማካተት አለበት ።ያ ካልሆነ ግን የሚኖረዉ ዉጤት ዉሱን ይሆናል።»
 »በኮምፓክት አፍሪካ»የታቀፉ ሀገራት ምርጫ ላይ ከሚነሳዉ ትችት ባሻገር ፣ በአፍሪቃ የሚገኙ አገር በቀል ኢንደስትሪዎችና ግለሰቦችን በዉጭ ባለሀብቶች እንዴት ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ በግልፅ  አለመቀመጡም ሌላዉ ችግር መሆኑን ቱቱ አጊያሬ የተባሉ የጋና ባለሀብት ይናገራሉ።
»ዓለማቀፋዊ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትን ያለ አካባቢያዊ ኢንድስትሪ እድገት ማካሄድ እስከመጨረሻዉ ማድረግ የሌለብን ነገር ነዉ። ምክንያቱም ስህተት በመሆኑ ነዉ።በአህጉሪቱ በንግድ ስራ ለመሰማራት የሚሻ ማንኛዉም አካል በቴክኒካዊ ስልጠና፣በቴክኒክ ባለሙያዎችና በቴክኖሎጅ ሽግግር ላይ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ መዘጋጀት አለበት የሚል ጠንካራ አቋም  አለኝ። ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ለሚቀጥሉት 5 እና 10 ዓመታት በአጋርነትም ይሁን በተናጠል እንዲሁም በባልደረባነት እነዚህን ነገሮች መስራት አለብን።»
እንደ ቱቱ አጊያሬ ይህ ኮምፓክት በአፍሪቃ ብቻ መታጠር የለበትም ።የአዉሮፓ ሀገራት ገበሬዎች ድጎማም ዉይይት ሊደረግበት ይገባል። በአፍሪቃ ግብርናና ወደ ፍሪቃ በሚገቡ ምርቶች ላይ ተፅዕኖ አለዉና።  የአፍሪቃ ገበሬዎች ምርቶቻቸዉን ለመሸጥ በአለም ገበያ ቦታ እንዲያገኙ ዉይይት ያስፈልጋልም ይላሉ። እሳቸዉ ይህን ይበሉ እንጅ በነገዉ የበርሊን ጉባኤ ቢያንስ በይፋዊ በመርሃ ግብር እነዚህ ጉዳዮች አልተካተቱም።

ምስል DW/I. Kaledzi
ምስል picture-alliance/dpa/M. Kappeler

ፀሀይ ጫኔ / ዳንኤል ፔልዝ

አዜብ ታደሰ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW