1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኮሮና ሥጋት በኢትዮጵያ የሥደተኛ መጠለያ ጣብያዎች

ዓርብ፣ መጋቢት 25 2012

የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣብያዎች ከፍተኛ አደጋ የተደቀነ ነዉ ተባለ። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በኢትዮጵያ በሚገኙ የስደተኛ መጠልያ ጣብያዎች ውስጥ የሚኖሩ ኤርትራውያንና ሶማልያውያን ስደተኞች የኮረና ቫይረስ ወረርሺኝ ስጋት እንዳለባቸው ይናገራሉ፡፡

Bildergalerie Flüchtlingscamp Tigray in Äthiopien
ምስል፦ Milena Belloni

የውኃና የፅዳት መጠበቅያ ቁሳቁስ እጥረት አለ

This browser does not support the audio element.

 

የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣብያዎች ከፍተኛ አደጋ የተደቀነ ነዉ ተባለ። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በኢትዮጵያ በሚገኙ የስደተኛ መጠልያ ጣብያዎች ውስጥ የሚኖሩ ኤርትራውያንና ሶማልያውያን ስደተኞች የኮረና ቫይረስ ወረርሺኝ ስጋት እንዳለባቸው ይናገራሉ፡፡ በኮምፖቹ የሚገኙ ስደተኞች እንደሚሉት በመጠልያዎቹ ያለው የውሃ እጥረት፣ የፅዳት መጠበቅ ቁሳቁስ ውሱንነት፣ የሕክምና ዝግጁነት ጉድለት እንዲሁም ሌሎች ችግሮች ስደተኞቹን ያስጨነቀ ሆንዋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ በበኩሉ በኢትዮጵያ በሚገኙ 28 የስደተኛ መጠልያ ጣብያዎች ውስጥ የቫይረሱ ወረርሺኝ እንዳይከሰት የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እየከወነ መሆኑ ይገልፃል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

 

አዜብ ታደሰ

 

ነጋሽ መሃመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW