የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት
ዓርብ፣ ጥር 15 2012ማስታወቂያ
የዓለም የጤና ድርጅት በእንግሊዘኛው ምህጻር WHO ኮሮና የተባለው ቫይረስ በቻይና ሰዎችን ቢገድልም በአሁኑ ደረጃ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ አዋጅ የሚያስወጣ አይደለም ሲል አስታውቋል። ያም ሆኖ የቫይረሱን ሥርጭት ለመከላከል መንግሥታት በአውሮፕላን ተጓዦች ላይ ቁጥጥራቸውን አጠናክረዋል።በተለይ ሳንባን ጉሮሮን እና የመሳሰሉትን የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ጉንፋን መሰል በሽታ የሚያስከትለው ይኽው ቫይረስ ከዚህ ቀደም በአፍሪቃ እና በአውሮጳ ተከስቶ እንደነበረ ተዘግቧል።ዘንድሮ በቻይና በሁዋን ከተማ ተከሰተ የተባለው የኮሮና ቫይረስ አዲስ የቫይረሱ ዓይነት ነው ተብሏል።የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ተጨማሪ ዘገባ አሰናድቷል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ