የኮሮና ተሕዋሲና የኢትዮ-ሱዳን ድንበር
ሐሙስ፣ መጋቢት 17 2012
ማስታወቂያ
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ኢትዩጵያ እና ሱዳንን የሚያገናኙ ስድስት በሮች መዘጋታቸውንና ጥብቅ ቄጥጥር እየተደረገ መሆኑንን የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ኩሙኒኬሽን ጉዳዩች ቢሮ አስታወቀ፡፡ በክልሉ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች የሠፈሩ ስደተኞችም እንዳይወጡና ባሉበት ሥፍራ ሆነው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ቢሮ ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ተናግረዋል፡፡በኒ ሻንጉል ጉሙዝ ርዕሠ-ከተማ አሶሳ ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሰዉ በኮሮና ተሕዋሲ ተለክፏል መባሉ የከተማይቱ ነዋሪዎችን አስግቷል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ