1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሮና ወረርሽኝና የቻይና ተፅዕኖ በአፍሪቃ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 19 2012

የቻይና እርዳታ ከአጋርነትና ከወዳጅነት ጋር የሚያያዙ የመኖራቸውን ያህል ከዕርዳታው ጀርባ ቻይና አጋጣሚውን በአህጉሪቱ ተፅዕኖ ለማሳደር እተጠቀመችበት ነው የሚሉም አሉ። በለንደን የምስራቃዉያንና ና የአፍሪቃ ጥናቶች ተቋም የፖለቲካና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር ስቴፋን ቻን እንደሚሉት እርዳታው የዲፕሎማሲ ግንኑነትን ለማጠናከር ያለመ ነው።

Äthiopien Addis Ababa | Coronavirus | Video Anruf aus Wuhan
ምስል imago images/Xinhua

የቻይና ተጽዕኖ በአፍሪካ

This browser does not support the audio element.


በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ቻይና የሚኖሩ አፍሪቃዉያን የዘረኝነትና የጥላቻ ድርጊቶች እያገጠማቸው መሆኑን ሲገልፁ ይሰማል ።በሌላ በኩል ሀገሪቱ በሽታዉን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ከአፍሪቃ ጋር ያላትን ትስስር የበለጠ እያጠናረከች ይመስላል።ለመሆኑ ቻይና ለአፍሪቃ የምታደርገው እርዳታ ምን አንድምታ አለው? ለተጨማሪ ዘገባው ፀሐይ ጫኔ።
የአፍሪካ ሀገራት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል በሚያደርጉት ጥረት ከቻይና ከፍተኛ ድጋፍ እያገኙ ነው ፡፡በቅርቡ ሀገሪቱ ሀኪሞቿን ወደ ኢትዮጵያና ቡርኪናፋሶ የላከች ሲሆን ከቻይና የሚነሱ ዕቃ ጫኝ አውሮፕላኖችም የፊት መሸፈኛዎችንና የመተንፈሻ መሳሪያዎችን ጭነው ነው ወደ አፍሪቃ የሚመጡት። ቻይናዊው ቱጃር ጃክ ማ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለበርካታ የአፍሪቃ ሀገራት የህክምና ቁሳቁሶችን ለግሰዋል።
ይህንን የቻይና እርዳታ ከአጋር ነትና ከወዳጅነት ጋር የሚያያዙ የመኖራቸውን ያህል ከዕርዳታው ጀርባ ቻይና አጋጣሚውን በአህጉሪቱ ተፅዕኖ ለማሳደር እተጠቀመችበት ነው የሚሉም አሉ።
በለንደን የምስራቃዉያንና ና የአፍሪቃ ጥናቶች ተቋም የፖለቲካና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር የሆኑት ስቴፋን ቻን እንደሚሉት እርዳታው የዲፕሎማሲ ግንኑነትን ለማጠናከር ያለመ ነው።
« የጭንብል ዲፕሎማሲ ልንለዉ እንችላለን።ምክንያቱም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን ያቀርባሉ። የመተንፈሻ መሳሪያዎችን እና የምርመራ ከረጢቶችን ያቀርባሉ።- በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገራት የነዚህ ሁሉ እጥረት አለ ። እናም ቻይናዉያን በጣም ጠቃሚ ስራ ነው የሰሩት።በእርግጥ ለቻይናም የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ይረዳታል።»
በሌላ በኩል በቅርቡ አፍሪቃውያን የኮሮና ወረርሽንን ያዛምታሉ በሚል በቻይናዋ ጓንዡ ከተማ መድሎዎና መገለል የደረሰባቸው ሲሆን አፍሪካዊያኑ አስገዳጅ የኮሮና ምርመራና ለ14 ቀናት በልየታ እንዲቆዩ ተደርገዋል ፡፡በጆሃንስበርግ የደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተቋም ባለሙያ የሆኑት ኮበስ ቫን ስታዴን እንደሚሉት ድርጊቱ ብዙ አፍሪቃውያንን ያስቆጣና የቻይናን ገፅታ ያበላሸ ነበር።
«ቻይና በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ከሚኖሩ አፍሪቃዉያን ስደተኞችን አያያዝ ጋር በተገናኜ ጥሩ ያልሆነ ምስል ነው ያላት። ይህ ሁሉ የሆነው በጓንዡ የኮቪድ-19 መስፋፋት ጋር ተያይዞ ነው።»እናም አፍሪቃዉያን ስደተኞች በአካባቢው ባለስልጣናት እንዲንገላቱ የሚያደርግ በአካባቢው መጥፎ ግንኙነትና መጥፎ አፈፃፀም ያለ ይመስላል።»
በገንዡ የተፈፀመው የዘረኝነት ድርጊት ብዙ አፍሪቃውያንን ከማስቆጣቱ ባሻገር መንግስታት በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ከስቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም ግፊት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።
ያም ሆኖ የቻይና መንግስት ጉዳዩን ሲያስተባብል ነው የቆየው ። ፕሮፌሰር ስቴፋን ቻን እንደሚሉት ግን የቻይና መንግስት ምንም እንኳ ችግሩን በይፋ ባይቀበለውም ከመጋረጃ ጀርባ ጉዳዩን ለማለዘብ እየጣረና አንዳንድ ርምጃዎችን እየወሰደ ነው። እርዳታውም ይህንን ገፅታ ለመቀየር እንደሚጠቅም አስረድተዋል።ያም ሆኖ የአፍሪቃዉያኑ እንግልት የሁለቱን ግንኙነት ይጎዳል ብለው አያስቡም።ምክንያቱም የአፍሪቃ መንግስታት ጉዳዩ ያን ያህል አላስቆጣቸውምና።
ቫን ስታዴን እንደሚሉት ግን ድርጊቱ የቱንም ያህል የሚያበሳጭ ቢሆን እንኳ በወረርሽኙ ሳቢያ የተፈጠረዉ የኢኮኖሚ ቀውስ አህጉሪቱ ከቻይና ጋር የበለጠ እንድትተባበር ያስገድዳል ።
«ኮሮናን በተመለከተ ቻይና ትልቅ አጋዥ ነች።ምክንያቱም «ዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ቀውስ የአፍሪቃ መንግስታትን ያላባቸውን የገንዘብ ብድር በተመለከተ ከቻይና ጋር እንደገና እንዲደራደሩ ያስገድዳቸዋል።በርካታ እርዳታ ከቻይና እየተገኜ ነው።ይህ ቀውሱን በመቀነስ ቻይና ዓለም አቀፍ የመሪነት ሚና ለመጫወት እየሞከረች የመሆኗ አንዱ አካል ነው ብየ አስባለሁ።»
ፕሮፌሰር እቴፋን በዚህ ይስማማሉ። አሁን በተከሰተው ቀውስ ምክንያት በአፍሪቃ የቻይና ተፅዕኖ ይቀጥላል።በሌላ በኩል በወረርሽኙ ሳቢያ ቻይናም ኢኮኖሚዋ በመጎዳቱ ሀገሪቱ ለአፍሪቃ ያላት ግልፅ መልዕክት ሁላችንም «አንድ ጀልባ ላይ ነን« የሚል መሆኑን ፕሮፌሰሩ ገልፀዋል።

ምስል picture-alliance/dpa/M. Hjaj
ምስል Getty Images/AFP/S Souici

ጸሐይ ጫኔ

ነጋሽ መሐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW