የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በድሬደዋ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 29 2013ማስታወቂያ
የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ እንደ አዲስ ስርጭቱ እየተባባሰ መቷል ያሉት የኮሮና ተሐዋሲ ዓይነት ላይ ሀገር አቀፍ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ነው የሚናገሩት። ወረርሽኙ ተስፋፍቶ በብዙዎች ላይ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ አስቀድሞም ኅብረተሰቡ እያሳየ ካለው መዘናጋት ወጥቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስበዋል፡፡
በአስተዳደሩ ዳግም በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት ያለበትን የኮሮና ተሐዋሲ ለማከም ቀደም ሲል የነበሩ የህክምና ተቋማት ዝግጅትን የማሻሻል ሥራ ተሰርቷል ያሉት ኃላፊዋ ከሁሉ በፊት ግን ቀድሞ ለመከላከል ሥራው ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት በሀገሪቱ ሦስተኛው ዙር የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እየጀመረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ መሆናቸውን ከቀናት በፊት ገልጿል።
መሳይ ተክሉ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ