1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  የኮንሶና የአሌ ጎሳን በማጋጨት የተጠረጠሩ ታሠሩ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 22 2013

የቢሮው ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዴ ዛሬ ለዶቼ ቬለ (DW) እንዳሉት ቢሮው ሰሞኑን ባካሄደው ካሰራቸዉ ተጠርጣሪዎች ዉስጥ ባለ ሥልጣናት፣ የመንግሥት ሠራተኞችና ገበሬዎች ይገኙበታል።

Äthiopien Das Hochland von Konso
ምስል picture-alliance/Mary Evans Picture Library/M. Watson

የኮንሶና የአሌ ማሕበረሰብን በማጋጭት የተጠረጠሩ ታሰሩ

This browser does not support the audio element.

የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የኮንሶና የአሌ ማኅበረሰብ አባላትን አጋጭተዋል፣ የሰዉ ሕይወትና ንብረት አጥፍተዋል ብሎ የጠረጠራቸዉን 310 ሰዎች አሰረ። የቢሮው ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዴ ዛሬ ለዶቼ ቬለ (DW) እንዳሉት ቢሮው ሰሞኑን ባካሄደው ዘመቻ ካሰራቸዉ ተጠርጣሪዎች ዉስጥ ባለ ሥልጣናት፣ የመንግሥት ሠራተኞችና ገበሬዎች ይገኙበታል። ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሁለቱ ማህበረሰብ አባላት መካከል ደም ሲያፋስስ የቆየው ግጭት ባለፈው እሁድ ባህላዊ የእርቅ ስረዓት ከተደረገ በኋላ የአካባቢው ሰላም እየተሻሻለ ነዉ። ዶቼ ቬለ (DW) ያነጋገራቸው የኮንሶና የአሌ ብሄር ባህላዊ ንጉሦችና የአገር ሽማግሌዎች «ከእርቅ ስረዓቱ በኋላ የንግድ ተቋማት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፣ ለወራት ተቋርጠው የከረሙ ገበያዎችም መቆም ጀምረዋል» ብለዋል።

ሸዋንግዛው ወጋየሁ 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW