1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮንጎ ግጭት፥ የሶማሊያ ጦርነት እና የዳርፉር ሠላም

ማክሰኞ፣ ኅዳር 9 2001

እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ከ1998 እስከ 2002 በተደረገዉ ዉጊያ እና ዉጊያዉ ባስከተለዉ በሽታና ረሐብ አራት ሚሊዮን ሕዝብ አልቋል።ብዙ ሚሊዮኖች ተሰደዋል።ወይም ተፈናቅለዋል። መቶ-ሺዎች ቆስለዋል።ሺዎች ተደፍረዋል

ሥደተኛዉምስል AP

የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ መንግሥት ጦርነ በመንግሥት ላይ ያመፁት ጄኔራል ሎራ ንኩንዳ የሚመሯቸዉ ሸማቂዎች ምሥራቃዊ ኮንጎ አዲስ የጀመሩት ዉጊያ የሚቆምበት ብልሐት አለምን ሲያነጋግር፥ የጀርመን ፖሊስ አንዲት የሩዋንዳ ባለሥልጣን ማሰሩ የሁለቱን ሐገራት ግንኙነት አሻክሮታል።የሶማሊያ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የፈረሙት የሰላም ዉል ገቢራዊ የሚሆንበት ቀን ሲናፈቅ አል-ሽባብ የተባለዉ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ርዕሠ-ከተማ መቅዲሾን ለመቆጣጠር መገሥገሱ ተስምቷል።በዚሕ መሐል ነዉ-የሱዳኑ ፕሬዝዳት ዑመር ሐሰን አል-በሽር ዳርፉር የሚዋጋ ጦራቸዉ ተኩስ እንደሚያቆም ያወጁት።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።እሁለት የሚከፈለዉ ትኩረት በአፍሪቃ ዝግጅታችን የአፍሪቃን መሰንበቻ ይቃኛል አብራችሁኝ ቆዩ።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW