የወለኔ ፓርቲ ቅሬታ
ረቡዕ፣ ሰኔ 19 2005ማስታወቂያ
የወለኔ ሕዝብ ሕገ-መንግሥታዊ መብቱ አልተከበረም፥ የሕዝቡ የመብት ጥያቄን በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፌደሬሽን ምክር ቤት ከዚሕ ቀደም ያሳለፈዉ ዉሳኔም እስካሁን ገቢራዊ አልሆነም በማለት የወለኔ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ።የፓርቲዉ ፀሐፊና ጊዚያዊ ሊቀመንበር ለጋዜጠኞች እንደነገሩት የወለኔ ሕዝብ ሕገ-መንግሥታዊ መብቱ እንዲከበር በመጠቁ ሰወስት ሰወስች ተገድለዉበታል፥ ሌሎች ስምንት ቆስለዉበታል።ባለፈዉ ሚዚያም የወለኔ ሕዝብ በሚኖርበት ወረዳ ምርጫ አልተደረገም።በጊዚያዊ ሊቀመንበሩ መግለጫ መሠረት በደሉን የሚፈፅመዉ የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድር ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ