የወላይታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ማስጠንቀቂያ
ቅዳሜ፣ ሰኔ 5 2013ማስታወቂያ
በወላይታ ዞን በምርጫው ሂደት ላይ እየተፈጸሙ ነው ባሏቸው ስህተቶች ምክንያት መጪው ምርጫ ፍትሓዊ እና ዴሞክራሲያዊ ይሆናል ብለው እንደማያምኑ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ወብን እና የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ወህዴግ ዛሬ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። ፓርቲዎቹ እንዳሉት ሁኔታው ካልታረመ በምርጫው የመሳተፋቸውን ጉዳይ እንደሚያጤኑ ገልጸዋል። የዞኑ የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት በበኩሉ በምርጫ ሂደቱ ላይ የተጠቀሱ ችግሮች እንዳሉ አምኖ ፤ ለችግሩ ገዢውን ፓርቲ እና ተፎካካሪዎችን ተጠያቂ አድርጓል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ታምራት ዲንሳ