1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወልቃይትና የራያን የማንነት ጥያቄ 

ሰኞ፣ ኅዳር 17 2011

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደግሞ የወልቃትና የራያ ህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግር እንጂ የማንነት ጥያቄ የለውም ብሏል፣ ያነጋገርናቸው የአካባቢውተወላጆችዎች የወልቃይትና የራያን የማንነት ጥያቄ ህወሓትም ዓለምም ያውቀዋል ሲሉ ተናገሩ፡፡

Äthiopien Kampagne Save Lake Tana
ምስል Kalkidan Tsena

የወልቃይትም ሆነ የራያ ህዝብ የመልካም አስተዳደር እንጂ የማንነት ጥያቄ የለውም

This browser does not support the audio element.

አዴፓ የተመሰረተበትን 38ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የሕዝቦችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ኃላፊነትና ተግባር ወቅቱ በሚጠይቀው መጠን በትጋት ይፈፅማል፡፡ እንዲሁም ከክልል ውጭ ያሉ ተወላጆችን መብት የማስጠበቅ እና የማረጋገጥ ተግባራትን ችግሮችን በሚፈታ መንገድ ለማከናወን እንደሚሰራም መግለጫው አመልክቷል፡፡ በተለይ ማንነትና የወሰን ጥያቄዎች መኖራቸውን የሚያምነው አዴፓ ከወሰንና ከአማራ ማንነት ጋር የሚነሱ ጥያቄዎችን ህዝብን በአማከለ መልኩ ለመፍታት ዝግጁነቱን አመልክቷል፡፡ የወልቃይትም ሆነ የራያ ህዝብ የመልካም አስተዳደር እንጂ የማንነት ጥያቄ የለውም በሚል ሰሞኑን የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ለዜና ሰዎች የሰጡትን መግለጫ ተከትሎ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች አንደገለፁት የራያም ሆነ የወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ በክልሉ መንግስት ይታወቃል፡፡ የራያ አካባቢ ተወላጅ የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰብአዊ መብትና የፌደራሊዝም ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ ምክትል ርዕሰ መስተዳሩ በሰጡት መግለጫ ዙሪያ አስተያየታቸውን ጠየቅኋቸው፣ የራያ ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ የታወቀና በርካታ ማሳያዎች እንዳሉት ያስረዳሉ፡፡ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የወልቃይት አካባቢ ተወላጅ ሲሆኑ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው፡፡ እርሳቸውም ቢሆን የወልቃይት የአማራነት ጥያቄ ዓለምም ያውቀዋል ሲሉ ነው አስተያየታቸውን የሰጡት፡፡ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ስለጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ የትግራ ክልል እንደመንግስት የራያም ሆነ የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ የለውም ዶ/ር ደብረፅዮን በጋዜጣዊ መግለጫ የተናገሩትም ስህተት የለበትም ብለዋል፡፡ በሌላ አካባቢ የማንነት ጥያቄ አለ ብሎ የሚያነሳው አካልም የወልቃትና የራያ አካባቢ ህዝቦች ወኪል እንዳልሆኑ በተጋጋሚ የተነገረና አሁንም የወልቃይትና የራያ የአማራነት ጥያቄ የለም ሲሉ ውድቅ አድርገዋል፡፡


ዓለምነው መኮንን


አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሠ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW