1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የወርቅ አምራች ማህበራት ፍቃድ ለምን ተሰረዘ ?

ሰኞ፣ መጋቢት 1 2017

ባለፉት ስድስት ወራት 150 ኪሎ ግራም ወርቅ ለማምረት ታቅዶ 75 ኪሎ ግራም ብቻ መገኘቱን የጠቀሱት የኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር «የአፈጻጸሙ ዝቅተኛ መሆን ማህበራቱ ምርታቸውን ለማዕከላዊ ገበያ ከማቅረብ ይልቅ ወደ ጥቁር ገበያ እንደሚያስገቡ አመላካች ነው፤በዚህም የ31 አምራች ማህበራትንና 1 የአቅራቢ ድርጅት ፍቃድ ሙሉ በሙሉ ተሰርዟል ብለዋል።

South West Ethiopia People Region Emblem
ምስል፦ South West Ethiopia People Region government Communication Affairs Bureau

የወርቅ አምራች ማህበራት ፍቃድ ለምን ተሰረዘ ?

This browser does not support the audio element.

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል  ከ60 በላይ በወርቅ ማምረትና ማቅረብ ሥራ የተሠማሩ ማህበራት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ፡፡ ከእነኝህ ማህበራት መካከል የሠላሳ  ሁለቱን የሥራ ፍቃድ ሙሉ በሙሉ መሰረዙን የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገ/ማሪያም ሰጠኝ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል ፡፡ በክልሉ ባለፉት ስድስት ወራት  150 ኪሎ ግራም ወርቅ ለማምረት ታቅዶ 75 ኪሎ ግራም ብቻ መገኘቱን  የጠቀሱት የኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር “ የአፈጻጸሙ ዝቅተኛ መሆን ማህበራቱ ምርታቸውን ለማዕከላዊ ገበያ ከማቅረብ ይልቅ ወደ ጥቁር ገበያ እንደሚያስገቡ አመላካች ነው ፡፡

ኤጀንሲው አሁን ለወሰደው የፍቃድ መሰረዝ እርምጃ ይህ ዋና ምክንያት ነው ፡፡ በአካባቢው ወርቅ እተመረተ እንደሚገኝ ኤጀንሲው በተለያዩ ጊዜያት ባደረጋቸው የመስክ ምልከታዎች እና  ከማህበራቱ ጋር ባደጋቸው ውይይቶች አረጋግጧል ፡፡ ነገር ግን የታቀደው የምርት መጠን ወደ ባንክ ሊመጣ ያልቻለው ወደ ጥቁር ገበያ ሥለሚገባ ነው የሚል ደምዳሜ በመድረሳችን ነው የመሰረዝ እርምጃውን የወሰድነው ፡፡ በዚህም መሠረት የ31 አምራች ማህበራትን እና 1 የአቅራቢ ድርጅት ፍቃድ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ ተደርጓል “ ብለዋል ፡፡

የአምራች  ማህበራቱ ቅሬታ

ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ድምጻቸውና የማህበራቸው መጠሪያ እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአምራች ማህበራት ሃላፊዎች ግን  የኤጀንሲው እርምጃ ነባራዊ ሁኔታውን ከግንዛቤ ያስገባ አይደለም ይላሉ ፡፡ የምርት አቅርቦቱን በዕቅዳቸው መሠረት መፈጸም ያልቻሉት በማምረቻ አካባቢዎች አልፎ አልፎ በሚስተዋለው የፀጥታ ስጋት የተነሳ ነው ብለዋል ፡፡በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የታገዱት የወርቅ አምራች ማህበራት

በተለይም በክልል ዋነኛ የወርቅ አምራች አካባቢ በሆነው የቤንች ሸኮ ዞን አምራቾች በተደጋጋሚ ለግድያ እና ለዘረፋ እየተዳረጉ ይገኛሉ ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ “ ይህ የምርቱን መጠንና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ባቀድነው የምርት መጠን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል ፡፡ ኤጀንሲው ፍቃድ ለመሰረዝ ከመወሰኑ በፊት ይህን ከግምት ማስገባት ነበረበት “ ብለዋል ፡፡

ጥቁር ገበያ

የማህበራቱ አስተያየት ከእውነት የራቀ ነው የሚለው ኤጀንሲው በበኩሉ ለምርቱ አለመቅረብ መንስዔው የፀጥታ ችግር ሳይሆን ሌላ ነው ይላል ፡፡ የወርቅ ምርት በሚመረትባቸው የተለያዩ የቤንች ሸኮ ወረዳዎች የማዕድን ምርት እንቅስቃሴ በፀጥታ ምክንያት ቆሞ እንደማያውቅ የሚናገሩት የኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገ/ማሪያም ሰጠኝ “ አልፎ አልፎ በመንገድ ላይ ተራ የዘረፋ ድርጊቶች እንዳሉ እናውቃለን ፡፡ ነገር ግን ምርት ሊያስተጓጓል ሚችል የፀጥታ ሥጋት የለም ፡፡ ዋናው ችግር ምርቱን በታማኝነት ለማዕከላዊ ገበያ አለማቅረባቸው ነው ፡፡ ከዚያ ይልቅ ወደ ጥቁር ገበያ የማድላት አዝማሚያዎች መኖራቸውን በክትትል አረጋግጠናል ፡፡ ለፍቃዳቸው መሰረዝ ምክንያትም ይኼው ነው ፡፡ በቀጣይ ቀሪ ማህበራት የምርት ሽያጫቸውን በባንክ በኩል ብቻ እንዲያከናውኑ ክትትል እና ድጋፍ  እየተደረገ ይገኛል  “ ብለዋል ፡፡በትግራይ ማንኛዉም አይነት የማዕድን ማውጣት ስራ ታገደ

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW