1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወባ በሽታ አሁም ጉዳት እያደረሰ ነው

ቅዳሜ፣ ኅዳር 22 2016

በቤጊ ሆስፒታል በአንድ ሳምንት ውስጥ 600 ናሙና ተወስደው 217 ሰው ላይ ወባ ተገኝቷል፡፡ ከእነዚህ መካከል 50 እና 60 የሚሆኑት ህመም የጠናባቸው ደግሞ ሆስፒታል ቆይተው የታከሙ ናቸው፡፡

Asiatische Tigermücke
ምስል H. Schmidbauer/blickwinkel/picture alliance

የወባ ወረርሽኝ ስጋት ደቅኗል

This browser does not support the audio element.

በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊና ቆንዳላ ወረዳ ውስጥ ወባ ስርጭት አሁንም መጨመሩንና ጉዳትም እያደረሰ እንደሚገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ ስርጭቱ ከገጠር በተጨማሪም በከተማም መበራከቱን አመልክተዋል፡፡ የቤጊ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ብርመዱ መኮነን  ባለፈው ሳምንት ወደ ሆስፒታል ከመጡ 600 መቶ ሰዎች መካከል 217 ሰዎች ላይ ወባ በሽታ መገኘቱን ጠቁሟል፡፡

የወባ በሽታ አሁም ጉዳት እያደረሰ ነው
በዝናብ መጠን መጨመርና የክረምት ወቅት መራዘም ጋር ተያይዞ በምዕራብ ወለጋ አንድ አንድ ወረዳዎች ውስጥ ወባ በሽታ ስርጭት መጨመሩን ነዋሪዎች ይገልጻሉ፡፡ በዞኑ ቤጊ ወረዳ ውስጥ የስርጭቱ መጠን አሁንም አለመቀነሱንና ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አስታውቋል፡፡ በወረዳው አሁንም በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ተገልጸዋል፡፡

በቤጊ ወረዳ ጢሎ፣ ያአ ማሳራ፣ ሎፒ እና ሌሎች ቦታዎች  ላይ ህብረተሰቡ በበጣም እየተጎዳ ነው፡፡ ድሮ በገጠር አካባቢ ብቻ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በከተማ ውስጥ በስፋት እየታየ ነው፡፡ በግጭት ምክንያት መንገድ ይዘጋል አቅርቦት የለም፡፡ ከባድ ዝናብ አልፎ አልፎ እጣለ በምርት ላይም ጉዳት አድርሷል፡፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ወረዳም የወባ ስርጭት ወደ ከተማም መዛመቱን አቶ ጉዲና ተሾሜ የተባሉ የወረዳው ነዋሪ ጠቁሟል፡፡ የወባ ስርጭት በተለየ መልኩ መስፋፋቱን የገለጹት ነዋሪው በአንድ አንድ አካባቢዎች የኬሚካል ሪጭት ተደርጎ የነበረ ሲሆን ለአጭር ጊዜ ቀንሶ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ባሁኑ ወቅት ተመልሶ በወረርሽኝ መልክ መጨመሩን አመልክተዋል፡፡ የመድሀኒት እጥረትም በአካባቢው እንዳለ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ የሰጡን የቆንዳላ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዩሰፍ ባርከሳ ባለፈው ሳምንት በወረዳው የወባ ስርጭት በከፍተኛ መጠን ጨምሮ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ``በዚህ 2 እና 3 ቀናት ውስጥ ቀንሷል፡፡ ባለፈው ሳምት ዝናብ ባለመቆሙ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ ነበር፡፡``

የወባ ትንኝምስል pzAxe/IMAGO

በቤጊ በአንድ ሳምንት 217 ሰዎች በወባ ተይዟል


የቤጊ ወረዳ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይረክተር ዶ/ር ብርመዱ መኮነን የወባ ስርጭትን ለመግታት በጎ አድራጊ ግለሰቦችና በመንግስት በኩል በርካታ የስራ ቁሳቁሶች ለሆስፒታሉ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ በቀን በትንሹ 60 ሰዎች በወባ በሽታ ታመው በሆስታሉ እንደሚታከሙ ገልጸው በሰው ህይወት ላይ የሚደርሰው ጉዳት በሆስፒታሉ ደረጃ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጋር ሲነጻጸር መቀነሱን አብራርተዋል፡፡ ሆኖም የወባ ስርጭት በወረርሽኝ መልክ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡

በወባ በሽታ የሚደርሰውን ሞት መቀነስ ተችሏል፡፡ ነገር ግን ወባ አሁንም እየታየ ነው፡፡ በቤጊ ሆስፒታል በአንድ ሳምንት ውስጥ 600 ናሙና ተወስደው 217 ሰው ላይ ወባ ተገኝቷል፡፡ ከእነዚህ መካከል 50 እና 60 የሚሆኑት  ህመም የጠናባቸው ደግሞ ሆስፒታል ቆይተው የታከሙ ናቸው፡፡  በሆስፒታል በሰው ህይወት ላይ በወባ የሚደርሰው ጉዳት በጣም ቀንሰዋል፡፡ 
በሐምሌ እና ነሐሴ ወር ውስጥበቤጊ ሆስፒታል ውስጥ 29 ሰዎች በወባ በሽታ ህይወታቸው ማለፉን መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ባወጣው መረጃም በክልሉ ወባ በ117 ወረዳዎች ውስጥ በወረርሽኝ መልክ መከሰቱን ገልጸዋል፡፡ 
ነጋሳ ደሳለኝ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW