1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወባ እና የደንጊ በሽታዎች ወረርሽኝ ስጋት በድሬዳዋ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 11 2015

ነዋሪዎች በአብዛኛው በችኩንጉንያ እንደታመሙ ቢገልፁም ኃላፊዋ በተለይ ወደ መንግስት ህክምና ተቋማት ከመጡ ሰዎች ተወስዶ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ውጤት መሰረት ምንም የችኩንጉንያ በሽታ ውጤት እንዳልተገኘ አስረድተዋል።አሁን ያለው የአየር ንብረት ሁኔታ ተደምሮ የወረርሽኙ መጠን እየቀነሰ መሆኑን ጠቅሰው ቀጣዩ ጊዜ ስጋት መሆኑን ተናገረዋል።

 ወይዘሮ ለምለም ወ/ሮ ለምለም በዛብህ የድሬዳዋ ጤና ቢሮ ኃላፊ
ለበሽታዎቹ ተቀራራቢ ምልክት የሆነው የትኩሳት ህመም ጋር በተያያዘ የሚታመሙ ሰዎች በየአካባቢው መታየታቸውን መሰረት በማድረግ ለቢሮው በቀረበ ጥያቄ መግለጫ የሰጡት የጤና ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ለምለም ለመከላከል እየተሰሩ ባሉ ስራዎች እና አሁን ላይ ያለው የአየር ንብረት ሁኔታ ተደምሮ የወረርሽኙ መጠን እየቀነሰ መሆኑን ጠቅሰው ቀጣዩ ጊዜ ስጋት መሆኑን ተናገረዋል።ምስል Mesay Teklu/DW

የወባ እና የደንጊ በሽታዎች ወረርሽኝ ስጋት በድሬዳዋ

This browser does not support the audio element.

በየጊዜው ወቅትን ተከትለው የሚቀሰቀሱት የወባ እና የደንጊ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክ መከሰታቸውን የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ  አስታውቋል። ቀጣዮቹ ጊዜያትም የወረርሽኙ ስጋት ያለባቸው በመሆኑ ከፍተኛ ዋጋ ሳያስከፍል ለመከላከል የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጿል።የመስተዳድሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በየአመቱ የክረምት እና በልግ ዝናብን ተከትሎ በድሬደዋ የሚከሰቱት የወባ እና የደንጊ በሽታዎች ዘንድሮ በከፍተኛ ደረጃ በጨመረ ቁጥር መከሰታቸውን ተናግረዋል። 

በአስተዳደሩ የገጠር ቀበሌዎች እንዲሁም ከአጎራባች አካባቢዎች የመጡ  የምግብ እጥረት ችግር ያለባቸው ሰዎች በተለይ ህፃናት ቁጥራቸው ከፍተኛ ሆኖ ማግኘራቸውን የተናገሩት ወ/ሮ ለምለም ከሚመለከታቸው አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የማከም እና የማዳን ስራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።ምስል Mesay Teklu/DW

ነዋሪዎች በአብዛኛው በችኩንጉንያ እንደታመሙ ቢገልፁም ኃላፊዋ በተለይ ወደ መንግስት ህክምና ተቋማት ከመጡ ሰዎች ተወስዶ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ውጤት መሰረት ምንም የችኩንጉንያ በሽታ ውጤት እንዳልተገኘ አስረድተዋል።ለበሽታዎቹ ተቀራራቢ ምልክትበድሬደዋ የደንጊ በሽታ ወረርሽኝ ተከሰተ የሆነው የትኩሳት ህመም ጋር በተያያዘ የሚታመሙ ሰዎች በየአካባቢው መታየታቸውን መሰረት በማድረግ ለቢሮው በቀረበ ጥያቄ መግለጫ የሰጡት የጤና ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ለምለም ለመከላከል እየተሰሩ ባሉ ስራዎች እና አሁን ላይ ያለው የአየር ንብረት ሁኔታ ተደምሮ የወረርሽኙ መጠን እየቀነሰ መሆኑን ጠቅሰው ቀጣዩ ጊዜ ስጋት መሆኑን ተናገረዋል።

የኮሌራ ወረርሽኝ

በድሬደዋ አስተዳደር ስር ከሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች አንዱ በሆነው የጀልዴሳ አካባቢ በቅርቡ የኮሌራ በሽታ ወረርሽኝ ተከስቶ እንደነበር ተገልጿል።ቢምቢ ወይም ትንኝ የሚያመጣቸው በሽታዎች ስጋት በድሬደዋይህ የተገለፀው በ2015 ዓ.ም በአስተዳደሩ በወረርሽኝ መልክ ያጋጠሙ በሽታዎችን አስመልክቶ የጤና ቢሮ በሰጠው መግለጫ ላይ ነው።

የጤና ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ለምለም ለመከላከል እየተሰሩ ባሉ ስራዎች እና አሁን ላይ ያለው የአየር ንብረት ሁኔታ ተደምሮ የወረርሽኙ መጠን እየቀነሰ መሆኑን ጠቅሰው ቀጣዩ ጊዜ ስጋት መሆኑን ተናገረዋል።ምስል Mesay Teklu/DW

ቁጥሩ ባይገለጥም በአካባቢው የተወሰነ የበሽታው ምልክት መገኘቱን የተናገሩት የጤና ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ለምለም  " ቶሎ ብለን ውሀን እንዲሁም ታማሚዎችን በማከም ምንም ዓይነት የከፋ አደጋ ሳይደርስ ተቆጣጥረነዋል" ብለዋል።በሌላ በኩል በቅርቡ በአስተዳደሩ የገጠር ቀበሌዎች እንዲሁም ከአጎራባች አካባቢዎች የመጡ  የምግብ እጥረት ችግር ያለባቸው ሰዎች በተለይ ህፃናት ቁጥራቸው ከፍተኛ ሆኖ ማግኘራቸውን የተናገሩት ወ/ሮ ለምለም ከሚመለከታቸው አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የማከም እና የማዳን ስራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።


መሳይ ተክሉ


ማንተጋፍቶት ስለሺ 
አዜብ ታደሰ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW