የፍርድ ቤት ዉሎ
ማክሰኞ፣ የካቲት 19 2011ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሙስና ወንጀል የተከሰሱትን የቀድሞዉን የብረታ ብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ የበላይ ኃላፊ የጄኔራል ክንፈ ዳኘዉንና የቴሌ ኮሚኒኬሽን ባለሥልጣን የነበሩትን የታናሽ ወንድማቸዉን የአቶ ኢሳያስ ዳኘዉን የክስ ሒደት ዛሬ ተመልክቷል። የፍርድ ቤቱ 15ኛ ወንጀል ችሎት በጄኔራል ክፍንፈ የክስ መቃወሚያ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ይዞት የነበረዉን ቀጠሮ ለሌላ ጊዜ አራዝሞታል። ፍርድ ቤቱ የአቶ ኢሳያስ ጠበቃን የክስ መቃወሚያ አድምጦ የአቃቤ ሕግን መልስ ለመስማት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ