1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወንዶች 5000 ሺ ሜትር የሩጫ ውድድር

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 23 2007

በዛሬው ዕለት ቤጂንግ ውስጥ በተከናወነው የወንዶች 5000 ሺ ሜትር የሩጫ ውድድር ብሪታኒያው አትሌት ሞ ራፋህ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሐጎስ ገብረ-ሕይወት ደግሞ የነሐስ ሜዳልያ አግኝቷል።

China Beijing IAAF Leichtathletik WM 5000 Meter Mo Farah
ምስል Getty Images/AFP/W. Zhao

[No title]

This browser does not support the audio element.

የብሪታንያው አትሌት ሞ ፋራህ በ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር አይበገሬ መሆኑን ዛሬ በድጋሚ አስመሰከረ። ቤጂንግ ውስጥ በተከናወነው የአምስት ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ሞ ፋራህ ዛሬ ሲያሸንፍ በኦሎምፒክ አለያም በዓለም አቀፍ ፉክክር በ5 ሺህ እና በ10ሺህ ሜትር በተከታታይ 7ኛ ድል ሆኖ ተመዝግቦለታል። ሞ ፋራህ በ5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር የዓለም ሻምፒዮና ለሦስተኛ ጊዜ በተከታታይ የወርቅ ተሸላሚ በመሆን ታሪክ ሠርቷል።
የ32 አመቱ ትውለደ-ሶማሊያ የብሪታንያ ዜጋ ሞ ፋራህ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2011 በዴጉ የ10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር በኢትዮጵያዊው አትሌት ኢብራሒም ጄላን ከተሸነፈ ወዲህ በዘርፉ የሚረታው አልተገኘም። በዛሬው የ5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ሐጎስ ገብረሕይወት ለኢትዮጵያ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝቷል። በዚህ ውድድር ኹለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነው የኬንያው አትሌት ካሌብ ምዋንጋኚ ንዲኩ ነው። አትሌት ዮሚፍ አጄልቻ በአራተኛነት አጠናቋል። ሌላኛው አትሌት ኢማነ መርጋ በ13ኛነት ውድድሩን ጨርሷል። በዛሬው የ5 ሺህ ሜትር የሩጫ ፉክክር በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ የቡድን ሥራ አለመታየቱ ተገልጧል።
በውድድሩ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሯጮች የተሳተፏ የነበረ ቢሆንም ድል ለማስመዝገብ አልቻሉም። ስለ ዕለቱ ውድድር ከፓሪሷ ወኪላችን ሐይማኖት ጥሩነህ ጋር የተደረገ የድምፅ ቃለ መጠይቅ ከዚህ በታች ያገኛሉ።

ሐይማኖት ጥሩነህ

ማንተጋፍቶት ስለሺ / ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW