1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዉህዳን እና ሕዳጣን ማሕበረሰቦች መብት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 13 2016

የኢትዮጵያ የዉህዳን እና የሕዳጣን ሁለንተናዊ ልማት ድርጅት አደረግሁት ባለው ጥናት ኢትዮጵያ ካቀፈቻቸው 86 የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ 36ቱ ውህዳን እና ህዳጣን ወይም "ማንነታቸው፣ ስማቸው፣ ባሕላቸው እና ታሪካቸው በፌደሬሽን ምክር ቤት እውቅና ያላገኘ" ናቸው ብሏል።

የኢትዮጵያ ገበሬ
የኢትዮጵያ ገበሬ ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የዉህዳን እና ሕዳጣን ማሕበረሰቦች መብት

This browser does not support the audio element.

በሀገሪቱ የሚካሄዱት የሀገራዊ ምክክር እና የሽግግር የፍትሕ ጥረቶች "ለዉህዳን እና ሕዳጣን ማሕበረሰቦችን" ተሳትፎ እና ፍላጎት ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠየቀ።እነዚህ የማሕበረሰብ ክፍሎች በሂደቶች ውስጥ በሦስተኛ ወገን ሳይሆን በቀጥታ ተሳታፊ እንዲሆኑ የጠየቀው የኢትዮጵያ የዉህዳን እና የሕዳጣን ሁለንተናዊ ልማት ድርጅት፤ በሂደቶቹ ልዩ ትኩረት ካላገኙ እና ተገቢው አያያዝ ካልተደረገላቸው የታሰበው ግብ ይሳካል ብለን አናምንም ብሏል።ድርጅቱ ይህንን ጥያቄውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በደብዳቤ መጠየቁንም አስታውቋል። 

 

የኢትዮጵያ የዉህዳን እና የሕዳጣን ሁለንተናዊ ልማት ድርጅት አደረግሁት ባለው ጥናት ኢትዮጵያ ካቀፈቻቸው 86 የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ 36ቱ ውህዳን እና ህዳጣን ወይም "ማንነታቸው፣ ስማቸው፣ ባሕላቸው እና ታሪካቸው በፌደሬሽን ምክር ቤት እውቅና ያላገኘ" ናቸው ብሏል።የኢትዮጵያ የዉህዳን እና የሕዳጣን ሁለንተናዊ ልማት ድርጅት ዉህዳን እና ሕዳጣን ሲል የሚጠራቸው በሕዝብ ብዛት አናሳ ቁጥር ያላቸውን፣ በእውቀት ከሌላው ዝቅ ብለው የሚገኙትን እና እጅግ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙትን "ማንነታቸው፣ ስማቸው፣ ባሕላቸው እና ታሪካቸው በፌደሬሽን ምክር ቤት እውቅና ያላገኘ" ናቸው። 

 

እነዚህ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተጋላጭ የሆኑ ፣አድሎ የሚደርስባቸው ፣የተበደሉ እና ለሌሎች አላግባብ ጥቅም ላይ የሚውሉ መሆናቸውን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደረሰ ዮሃንስ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።"የእነዚህ ማሕበረሰቦች ቁልፍ ችግር በእውቀት፣ በቁጥር ብዛት እና በኢኮኖሚ እጅግ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ከመገኘታቸው የተነሳ ሁለንተናዊ የሆነ ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ ልቦናዊ ቀውስ ውስጥ ያሉ ናቸው"።ድርጅቱ አደረግሁት ባለው ጥናት ሀገሪቱ ካቀፈቻቸው 86 "የማህበረሰብ ክፍሎች" ውስጥ 36ቱ ዉህዳን እና ህዳጣን ናቸው ያሉት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ማህበራዊ መበደል ብሎም ራስን የመግለጽ ችግር ያለባቸው መሆኑን በምሳሌ ጭምር አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ምስል Seyoum Getu/DW

 

በሀገሪቱ እየተካሄዱ ያሉት የሀገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትሕ ጥረቶች "ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተከሰቱ ያሉትን አስከፊ ግጭቶች እና ጦርነቶች በማስወገድ የታሰበውን ሰላም ለማስጠበቅ የሚያስችሉ መሆን አለባቸው ብሎ እንደሚያምን ድርጅቱ ገልጿል። በዚህ ሂደት ግን በተገቢው ሊወከሉ ይገባል ሲሉ የድርጅቱ ኃላፊ ገልፀዋል።"ማንነታቸው በፌደሬሽን ምክር ቤት ታውጆ ሙሉ ማን እንደሆኑ አይታወቅም"። ሌሎች አካላት በሚጠራቸው መጠርያ እና ፣ እንዲህ ናችሁ ብለው በሚሏቸው መለያ እና ማንነት ነው የሚታወቁት"።

ዉህዳን እና ሕዳጣን የተባሉት ማሕበረሰቦች በአኗኗራቸው "ግራ የተጋባ ስብዕና ያላቸው ፣ ዝቅተኛ ትምህርት ደረጃ ያላቸው እና ከባድ ድህነት ውስጥ ያሉ" ሲሆን ለሁሉም ዓይነት የሕይወት ችግሮች የተጋለጡ እንዲሁም የነሱ የሆነውን ሁሉ ወደ ጎን በመተው ብዙኃነት ያላቸውን ግለሰቦች እና ቡድኖች ፍላጎት እንዲከተሉ የሚገደዱ መሆናቸውን ለመብታቸው መከበር ጥረት እያደረገ ያለው ድርጅት አስታውቋል።

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW