1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዋጋ ንረት፦ ገፊ ምክንያቶች፣ የብሔራዊ ባንክ እርምጃ እና የወደፊት ሥጋቶች

እሑድ፣ መስከረም 29 2015

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሲገሰግስ የታየው የዋጋ ንረት ገፊ ምክንያቶቹ ምንድን ናቸው? የብር የምንዛሪ ተመን መዳከም ለዋጋ ንረት ምን አይነት ሚና ተጫወተ? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እርምጃዎች ምን ፈየዱ? በዚህ ውይይት አቶ አቢስ ጌታቸው፣ ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ እና ዶክተር ቀልቤሳ መገርሳ ተሳትፈዋል።

Äthiopien | Traditioneller Markt in Debre Markos
ምስል DW/E. Bekele

የዋጋ ንረት፦ ገፊ ምክንያቶች፣ የብሔራዊ ባንክ እርምጃ እና የወደፊት ሥጋቶች

This browser does not support the audio element.

ጦርነት፣ ግጭት፣ የበጀት ጉድለት፣ የብር የምንዛሪ ተመን መዳከም በርትቶ በታየበት በ2014 በየወሩ የነበረው የዋጋ ንረት ከፍተኛ ነበር። የምግብ ዋጋ ንረት በየካቲት ወር ከ2013 ጋር ሲነጻጸር በ41.9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት መረጃ መሠረት በ2014 ሰኔ ወር በ38 በመቶ ገደማ ከፍ ብሎ ነበር።

ባለሙያዎች እንደሚሉት የምርቶች እጥረት፣ የነዳጅ ዋጋ መጨመር፣ የውጪ ምንዛሪ እጥረት፣ የወጪ እና ገቢ ንግድ ሚዛን መጓደል፣ በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ ገበያ የታዩ ቀውሶች የዋጋ ንረቱን ካባባሱ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። 

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ተግባራዊ በሚያደርገው የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር ሳቢያ ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን በተከታታይ መዳከምም የዋጋ ንረቱን በማባባስ የራሱን ሚና እየተጫወተ ነው። ይኸ ውይይት በተደረገበት ዕለት መስከረም 26 ቀን 2015 ባንኮች አንድ የአሜሪካ ዶላር በ52 ብር ከ60 ሳንቲም ገደማ ገዝተው በ53 ብር ከ70 ሳንቲም ገደማ ይሸጣሉ። ይሁንና በትይዩው ገበያ አንድ ዶላር  ከ90 እስከ 110 ብር ድረስ እንደሚመነዘር ዶይቼ ቬለ ለመገንዘብ ችሏል። 

ይኸ የውይይት መሰናዶ የዋጋ ንረትን ገፊ ምክንያቶች፣ የብሔራዊ ባንክ እርምጃ እና የወደፊት ሥጋቶች ይፈትሻል። የምጣኔ ሐብት ባለሙያው አቶ አቢስ ጌታቸው፣ የኢትዮጵያን ኤኮኖሚ በቅርበት የሚከታተሉት የፋይናንስ ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ እና በብሪታኒያው የልማት ጥናት ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ቀልቤሳ መገርሳ በዚህ ውይይት ተሳትፈዋል። 

ሙሉ ውይይቱን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ

እሸቴ በቀለ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW